1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ካናዳ ለጓንታናሞ እስረኛ ካሳ ከፈለች

ሐሙስ፣ ሐምሌ 6 2009

የካናዳ መንግሥት ለቀድሞው የኧል-ቃዒዳ አባልና ለአንድ የአሜሪካ ወታደር መሞት ተጠያቂ ለኾነው ኦማር ከድር የ10.5 ሚሊየን ዶላር ካሣ መስጠቷ ተነገረ፤ ውሳኔው ከፍተኛ ውዝግብ ቀስቅሷል፡፡ ካሣው ኦማር በታዳጊነት ዕድሜው በአፍጋኒስታን የአል-ቃዒዳ ነው፤

https://p.dw.com/p/2gUcI
Omar Khadr / Guantanamo / Kindersoldat
ምስል AP

Ber.Toronto(Kanada entschuldigt den Gefangenen von Guantanamo Bay Omar Khadr) - MP3-Stereo

 

ተብሎ በሚታመን የጦር ሰፈር ውስጥ በአሜሪካ ልዩ ኃይሎች ተይዞ ለ10 ዓመታት በጓንታናሞ ወህኒ ቤት ባሳለፈው ስቃይ የሀገሩ የካናዳ መንግሥት ሊታደገው ባለመቻሉ እንደኾነ መንግሥት ገልጧል፡፡ ኦማርም የ20 ሚሊዮን ዶላር ክስ መንግሥት ላይ መሥርቶ ከጎርጎሮሳዊው 2014 ጀምሮ በፍርድ ቤት ሲሟገት ነበር፡፡  ውሳኔውን ሁለቱ ዋነኛ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ጨምሮ በብዙዎች ተተችቷል፡፡  ከቶሮንቶ ዝርዝር ዘገባ ልኮሎናል። 


አክመል ነጋሽ

አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ