ካራቱሪ የህንድ ገበሬዎች የማስፈር እቅድ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 14 2004ማስታወቂያ
በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ጋምቤላ በርካሽ የሊዝ ኪራይ በወሰደዉ አንድ መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ዉስጥ በሃያ ሺዉ ሄክታር ላይ የህንድ ገበሬዎችን ለማስፈር መዘጋጀቱን ለአንድ ጋዜጣ መግለፁን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዘግቧል። የግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ ካራቱሪ ለመዋዕለ ንዋይ ፍሰት በሊዝ በተሰጠዉ መሬት ላይ ሰፈራ ማካሄድ እንደማይቻል፤ ከህንድም ገበሬዎች ለማስመጣት ስለመጀመሩ አላስታወቀም ሲል ለዶቼ ቬለ አስታዉቋል።
ታደሰ እንግዳዉ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ