ከጥቃት የተረፉት ጥገኝነት ጠያቂ
ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2011ማስታወቂያ
በ2008ዓ,ም ኢትዮጵያ ውስጥ በቀድሞው የደህንነት ኃላፊ የተሰጠኝን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል ርምጃ የመውሰድ ትዕዛዝ ተግባራዊ ባለማድረጌ ድንገት ታፍኜ ከአራት ወራት በላይ በእስር ቆይቼ ነበር ይላሉ መጠሪያ ስማቸውን እንደለወጡ የሚናገሩት ስደተኛ። በመጀመሪያ ማዕከላዊ ከዚያም ወዳላወቋቸው ወደተለያዩ እስር ቤቶች ፊታቸው እየተሸፈነ በመዘዋወር ቁምስቅል እንደተፈፀመባቸው ይዘረዝራሉ።
እስር ላይ ሆነው ፍርድ ቤት በተወሰዱበት ወቅት ድንገት ባገኙት አጋጣሚ ለማምለጥ እና ከሀገር ለመውጣት የቻሉት በስደት ስማቸው ቴዎድሮስ የተባሉት ሌተናል ኮሎኔል የሊቢያን በረሃ፤ ቀጥሎም የሜዲትራኒያን ባሕር አቋርጠው ጀርመን ቢገቡም «አሳዳጆቼ» የሚሏቸው የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግሥት የደህንነት ባልደረቦች ማስፈራራት እና ዛቻ አልተለያቸውም። በዚህም ሳይበቃ ከሰሞኑ ሊሰነዘርባቸው ከታቀደ የግድያ ሴራ ለጥቂት መትረፋቸውንም ያስረዳሉ። ጉዳዩን በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ በማመልከት ጥበቃ እና ክትትል እየተደረገላቸዉ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል። ዝርዝሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ