1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጣሊያን ወደ ስዊድን የተላኩ ኤርትራውያን

ዓርብ፣ መስከረም 28 2008

ስዊድን በዛሬው ዕለት ከጣሊያን 19 ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሀገሯ ማስመጣቷ ተገለጠ። የአውሮጳ ሕብረት ስደተኞችን በአባል ሃገራቱ ለማከፋፈል በቅርቡ ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/1Glbo
Flüchtlinge aus Eritrea werden vom Flughafen Rom-Ciampino nach Schweden gebracht
ምስል Reuters/R. Casilli

[No title]

ኤርትራውያኑ ስደተኞችን የጫነው የጣሊያን ፖሊስ አውሮፕላን ከመዲናዪቱ ሮም በመነሳት ሰሜናዊ ስዊድን ውስጥ ወደምትገኘው ሉሌያ የተባለች አካባቢ መብረሩ ተዘግቧል። ስደተኞቹ ስዊድን ውስጥ ተመዝግበው የጥገኝነት ጥያቄያቸው በሒደት መታየት እንደሚጀምርም ተገልጧል። .የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴዎድሮስ ምሕረቱ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ቴዎድሮስ ምሕረቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ