1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጋምቤላ ከታገቱት 14 መመለሳቸው

ሰኞ፣ ግንቦት 1 2008

ተመለሱ ስለተባሉት ህጻናት የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ህጻናቱን የማስመለሱ ሥራ ውጤት እያመጣ መሆኑን ከመናገር ውጭ ዝርዝር ሁኔታዎችን አልገለጹም ።

https://p.dw.com/p/1Ikeh
Äthiopien, Massaker in der Region Gambela
ምስል DW/Y. Gebregziabeher

[No title]


ከሶስት ሳምንት በፊት ከደቡብ ሱዳን መጡ በተባሉ የሙርሌ ጎሳ አባላት ከጋምቤላ ከታገቱት ህጻናት መካከል 14ቱ መመለሳቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ዘግበዋል ። ተመለሱ ስለተባሉት ህጻናት የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ህጻናቱን የማስመለሱ ሥራ ውጤት እያመጣ መሆኑን ከመናገር ውጭ ዝርዝር ሁኔታዎችን አልገለጹም። ሃላፊው ህጻናቱን ማስለቀቁ የዘገየው ጉዳት ሳይደርስባቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ በሚደረገው ጥንቃቄ መሆኑን አስታውቀዋል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ