1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጊኒ ቦክሳይት ተጠቃሚው ማነዉ?

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2005

ምዕራብ አፍሪቃዊትዋ ጊኒ-ኮናክሪ በተፈጥሮ ሃብት የታደለች ሀገር ናት። በዓለም ዙርያ ከርሰ-ምድር ዉስጥ ከሚገኘዉ ቦክሳይት ማለት የአልሙንዩም ንጥረ ነገርን የያዘዉ ድንጋይ ሁለት ሶስተኛዉ በጊኒ ከርሰ-ምድር ዉስጥ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/17WeL
ምስል DW/B. Barry

የአልሙንየምን በዉስጡ የያዘዉ ቦክሳይት የተሰኘዉ ንጥረ ነገር በዓለማችን ገበያ ላይ በተለይም በመኪና ምርት ኢንዱስትሪ እጅግ ተፈላጊ  ነዉ። ግን ከጊኒ ይህን ለዉጭ ገበያ ለማቅረብ 14 ሚሊዮን ህዝቧ ብዙም አይታየዉም። ምክንያቱ ሀገራቸዉ አሁንም እጅግ ደሃ ከተሰኙት 20 የዓለም ሀገራት አንዷ በመሆንዋ ነዉ። የሀገሪቱ ፕሪዚደንት አልፋ ኮንዴ በአዲሱ የጥሪ ሃብት  ፖሊቲካ የሀገራቸዉን ገፅታ ለመቀየር ተነስተዋል። ከሁለት ዓመት ጀምሮ ስልጣን ላይ ያሉት ፕሪዚደንት አልፋ ኮንዴ በዲሞክራሲ መንገድ የተመረጡ የመጀመርያዉ የጊኒ ፕሪዝዳንት ናቸዉ።  የዶቼ ቬለዉ  ቦብ ቤሪ ከጊኒ መዲና ኮናክሪ 150 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ሚገኘዉ ዴቤሊን የማዕድን ማዉጫ ተጉዞ ቦክሳይት ማዕድንን ለማዉጣት የሚደረገዉን ትግል እና ከንጥረ ነገሩ ማን ተጠቃሚ መሆኑን ያስቃኘናል።

Fotograf ist Bob Barry, freier DW-Mitarbeiter Aufnahmedatum: 06.09.12 Die Bilder wurden alle aufgenommen in der Mine von Debélén in der Provinz Kindia in Guinea-Conakry. Zu sehen sind im Porträt Schichtleiter James Camara und Produktionsleiter Mamadou Barry.
ምስል DW

ዴቤሊን የማዕድን ማዉጫ በምዕራባዊ ጊኒ ኪንዲአ ክፈለ-ግዛት በሚገኝ አነስተኛ ቦታ ላይ ይገኛል። የማዕድን ማዉጫ አካባቢ የማንግሮቭን እና የማንጎ ዛፍ በቅሎአል። የመሪቱ አፈር ቀይ እና የተቃጠለ ዓይነት ሽታም አለዉ። በዝያ ነዉ የአልሙንዩም ንጥረ ነገርን የያዘዉ ቦክሳይት የጊኒ እጅግ ግዙፉ የተፈጥሮ ሃብት ተደብቆ የሚገኘዉ።  

ከሃያ አመታት በላይ የሩስያ ኩባንያዎች በሀገሪቱ ንጥረ ነገሩን ከከርሰ ምድር በማዉጣት ላይ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት ሩሳል የተሰኘዉ የሞስኮዉ ኩባንያ ቦታዉ ላይ ይገኛል።መሃመድ ሲላ በዚህ ማዕድን ማዉጫ ዉስጥ መስራት ከጀመረ አምስት ዓመታትን አስቆጥሮአል። «የምርት ክፍል ሃላፊ ነኝ። የማዕድን ማዉጫዉን ማሽን በታቀደዉ ርቀት እና ዕቅድ መስራቱን እቆጣጠራለሁ። »

ሲላ ብርሃን የሚያንፀባርቅ ቢጫ የመከላከያ ሰደርያ  እና በአደጋ ግዜ የራስ ቅል መከላከያ ብርቱካናማ  ቆብ አጥልቆአል። የሀገሪቱ ሃብት አልሙንዩም ንጥረ ነገርን የያዘዉ ቦክሳይት ማዕድንን ከሚገኝበት አካባቢ የመጣ በመሆኑም የማዕድኑ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆንን ይፈልጋል።  

Projekt: Jagd auf Rohstoffe Infografik Exporte Bauxit amharisch AMH

«ደምወዙ በቂ አይደለም። በቤተሰብ ዉስጥ እጅግ ችግር አለብን። በወሩ መጨረሻ የሚሰጡን ሁሉ ያልቃል ፤ በቂ አይደለም»

በዚሁ የማዕድን ማዉጫ የፈረቃ ሃላፊ የሚሰራዉ ወጣት ጀምስ ካማራ ሁኔታ ደግሞ ከዚህ ለየት ያለ ነዉ። ጀምስ የከፍተኛ ትምህርቱን በሞስኮ ሲያጠናቅቅ፤ አንድ የጊኒ ፍራንክ እንኳ አልከፈለም። ይኸዉ የሩስያ ኩባንያ ነዉ የነፃ ትምህርት ዕድልን ሰቶት ትምህርቱን አጠናቆ ወደ አገሩ ለመመለስ የበቃዉ። ጀምስ ካማራ ዛሪ በ 32 ዓመቱ የመጀመርያ ስራዉን በሩስል የማዕድን ማዉጫ ይዞ፤ በቀን ዉስጥ ያለዉን የስራ ሂደት ይቆጣጠራል።  ካማራ አባቱ በዚሁ ማዕድን ማዉጫ ይሰሩ እንደነበር እንዲህ ያስታዉሳል።

«ሩሳል ለሰራተኞቹ በፃፈዉ ደብዳቤ፤ ለሰራተኞቹ  ልጆች አንድ ዉድድር እንደሚያደርግ አስታወቀ። በዚህ ዉድድር የሂሳብ፤ የፊዚክስ እና የኩሚስትሪ ፈተናን ማለፍ ነበረብን። ከዝያም የነፃ ትምህርት ዕድልን ያገኙ አምስት ልጆች  የተመረጡት።»

ከዛሪ አንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ወጣቱ የፈረቃ ተቆጣጣሪ ሲሆን፤ ከከርሰ ምድር የሚወጣዉን ቦክሳይት ማዕድን እንዲት እንደሚወጣ እና እንዴት በተሽከርካሪ ተጭኖ እንደሚመላለስ ይቆጣጠራል።እንደ ሩሳል የማዕድን ማዉጫ ኩባንያ ገለፃ ቦክሳይትማዕድን በዓለም ገበያ ላይ በመርከሱ ምክንያት፤ ማዕድኑን የማዉጣቱን  ስራ ቀለል ማድረግ እንደሚፈልግ ይገልጻል። ስለዚህም ኩባንያዉ ከጀርመን ተንቀሳቃሽ የመቆፈርያ እና የመዛቅያ ገልባጭ መኪና ማሽንን ገዝቶአል።

የፈረቃ ተቆጣጣሪዉ ካማራ በኩራት ፈገግታ አንዱን ገልባጭ በማሳየት ማሽኑ መሪት በመቆፈር በመቦርቦር እና በመዛቅ መሪቱን እንደሚገለባብጥ  ይገልጻል። ይህ ገልባጭ መኪና ማዕድኑን ከመሪት ዝቆ በማዉጣት ሰባብሮ መኪና ላይ በመጫን በአንድ ግዜ ሶስት ስራን በፍጥነት ያከናዉናል። «ይህ ማሽን በአንድ ሰዓት ዉስጥ 750 ቶን  መቆፈር ይችላል-አለት ድንጋዩን አስወግደን ሰባት ገልባጭ መኪና ሙሉ ማዕድን መጫን እንችላለን።» በዚህ ዘዴ ሩስል የማዕድን ማዉጫዉን ሰዓት እስከ ሰባ በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ካማራ ይናገራል። በዚህ ዉጤትም  ወደ 300 ያህል የማዕድን ማዉጫ ኩባንያዉ ሰራተኞች የስራ ቦታቸዉን ማጣታቸዉን የአገሪቱ ሰራተኛ ማህበራት ይገልጻሉ። በዚህም ሰራተኛዉ አዲሱንና ፈጣኑን የመቆፈርያ ገልባጭ መኪና  እጅግ ሲጠላ፤ የሩሳል አስተዳዳሪዎች ግን ይወዱታል።  «አሁን በዝናባማ ወራት ቦክሳይት ማዕድኑ ከአፈር ጋር ተደባልቆስለሚጨቀይ  የመቆፈርያ ማሽን ለመጠቀም ባጣም አዳጋች ሁኔታን ፈጥሮብናል። ስለዚህም ማሽኑ ቆፍሮ ድንጋዩን እያወጣ፤ በትንሽ በትንሹ ሲባብሮ ፤መኪና ላይ ሲጭን፤ ማሽን ዉስጥ የጨቀየዉ ድንጋይ እንዳይወተፍ፤ በማሽኑ ላይ ያላማቋረጥ ወሃ እናፈሳለን።»  ትንሽ ሜትር ራቅ ብሎ በጥሞና ለሰራተኞች ገለጻ በመስጠት ላይ ያለዉ ማማዱ ቤሪን እናገኛለን። ማማዱም እንዲሁ በጊኒ መንግስት በኩል በተሰጠዉ የነፃ ትምህርት ዕድል፤ በሩስያ ሳንት ፒተርበር ዩንቨርስቲ በማዕድን ፍልጋ ሞያ ትምህርቱን ጨርሶ በጊኒ የማዕድን ማዉጫ ዉስጥ ከሚገኙት ወጣት ስራ አስኪያጆች መካከል ተሰልፎአል። ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላም በሩሳል የማዕድን ማዉጫ አንድ ሩስያዊ የስራ አስኪያጅን ተክቶ ምርት ክፍሉን በማስተዳደር ላይ ይገኛል። «እዚህ ስራ እንተቀጠርኩ በቂ ደምወዝ አላገኝም ነበር። አሁን ግን በቂ የስራ ልምድ ስላለኝ  ደምወዜ ጨምሮአል፤ በአሁኑ ሰዓት በተሟላ ስሜትም አለኝ። ባገኘሁት ገንዘብ ሚስት አግብቼ፤ አሁን አንዲት ሴት ልጅ አለችኝ።  አሁን በዘመናዊዉ የማዕድን ማሽን ሳይሆን በባህላዊ መንገድ ድንጋይ ወደ ሚፈለጥበት የማዕድ ማዉጫ ስፍራ ደግሞ እናመራለን። ቦታ በመኪና የደቂቃዎች መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል።በማዕድን ማዉጫዉ ስፋራ የለዉ አየር የተቃጠለ የመሪት ሽታ የቀላቀለዉ ከባድ እና መሪቱ ጭቃማ ነዉ። አንድ ሰዉ ወደ ማዕድን ማዉጫዉ ጣርያ መሄድ እንዳለብን ነገረን እና ከደቂቃዎች በኋላ ጥቁር የለበሰዉ ኢንጂኔር፤ ጎኒካ ቶሪ  ድማሚት አፈነዳ።  ከፍንዳታዉ በኋላ ጥቁር እና ፍም የመሰለ ጭስ ድንጋዩን አለበሰዉ። ኢንጂኔሩም በኩራት ስራዉን እንዲህ አሳየን።

Die Bilder wurden alle aufgenommen in der Mine von Debélén in der Provinz Kindia in Guinea-Conakry. Fotograf ist Bob Barry, freier DW-Mitarbeiter Aufnahmedatum: 06.09.12
ምስል DW/B. Barry
Fotograf ist Bob Barry, freier DW-Mitarbeiter Aufnahmedatum: 06.09.12 Die Bilder wurden alle aufgenommen in der Mine von Debélén in der Provinz Kindia in Guinea-Conakry. Zu sehen sind im Porträt Schichtleiter James Camara und Produktionsleiter Mamadou Barry.
ምስል DW

«ከስምንት አመት ጀምሮ ድማሚት የሚቀበርበትን ጉድጓዶች በተመለከተ ሃላፊነቱን ወስጄ እሰራለሁ። ይህ ስራ በርግጥ ለህይወት እጅግ አደገኛ ነዉ። ዓለት ድንጋዪ በአንድ በኩል ብቻ ከፈነዳ፤ ጭንቅላትህን ሊያገኝህ ይችላል። ፍንዳታዉ ከተከናወነና አለቱ ከተሰባበረ በኋላ መኪኖች መጥተዉ የተሰባበረዉን ድንጋይ ሰብስበዉ ለፋብሪካ ያቀርባሉ» ቶሪ የጠቀሱት ፋብሪካ እዝያዉ ዓለቱ በተሰባበርት አካባቢ የሚገኝ ፋብሪካን ነዉ። በፋብሪካዉ ትልልቁ ዓለት በትንሽ ትንሽ እስኪሰባበር ብዜ ግዜን ይወስዳል። ለዝያም ነዉ ሩሳል የማዕድን ማዉጫ ዘመናዊዉን የድንጋይ መሰባበርያ ገልባጭ መኪናን መጠቀም የጀመረዉ።  ማዕድኑ የያዘዉ ድንጋይ ከሚሰባበርበት ቦታ ወጣ ብሎ ግቢዉ ደጃፍ በሚገኘዉ የመግብያ መቆጣጠርያ አካባቢ ሰራተኞች ሲጋራ፤ ዉሃ አልያም ፤የሚበላ ዳቦ መግዛት ይችላሉ። አንድ ወጣት አንድ የማንጎ ዛፍ ስር ካለ አነስ ያለ ግንብ ላይ ተቀምጦአል። አሴኒ ካማራ ይባላል፤ በእቃ መጫኛ ባቡር ሊጫን የተዘጋጀዉን የቦክሳይትማዕድንን የያዘዉን የተሰባበረ ድንጋይ በቀዝቃዛ አስተያየት ይመለከታል። ካማራ በአካባቢዉ ከሚገኘዉ እጅግ ብዙ ስራ አጥ ቡድኖች መካከልም አንዱ ነዉ። እንደሱ አባባል ጥሪ ሃብትን በምትሰጠዉ በሱ የትልዉድ መንደር ስራ ማግኘት አለመቻሉ፤ ሊገባዉ የማይችል ጉዳይ ነዉ።

«በደብሊን የሚገኙ በርካታ ወጣቶች አሁንም ስራ ማግኘት አልቻሉም፤ ሁሉም ስራ አጥ ወጣት በአንድ ሞያ የሰለጠ ነዉ። ሩሳል ስራ ለማግኘት እንዲረዳን እንጠይቃለን»

Mine von Debélén Guinea-Conakry
ምስል DW/B. Barry

በትዉልድ ቀየ አካባቢ ስራን ማግኘት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አልሴኔ ይገላጻል። እንደ በርካታ የጊኒ ተወላጆች የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ሀገርን ጥሎ ላለመሄድ ወደ አዉሮጳ ላለመሰደድና በግዴታ ስራን ማግኘት አስፈላጊ ነዉ።

ሌላዉ የጊኒ ዜጋስ እንዴት ይኖራል? ሀገራቸዉ በተፈጥሮ ከሰጠቻቸዉ ጥሪ ሃብት ምንስ ይተርፋቸዋል?ጥሪ ማዕድኑ ከሚወጣበት የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ አድርገን 200, 000 ህዝብ በሚኖርባት የአዉራጃ  ዋና  ከተማ ኪንዳን  ጎበኘን። ከተማዋ በአረንጓዴ ሰንሰለት ተራራ ተከባ ከሩቅ ትታያለች። ከተማዉ መግብያ ላይ በሚገኘዉ በአንድ ያረጀ ህንጻ ዉስጥ ገባን። ወደ ቢሮዎቹ ዘልቆ ሲገባ ኮሪደሩ በጨለማ ተዉጦአል፤ ኤሌትሪክ በመጥፋቱ ነዉ።  በቢሮ ዉስጥ እድሜን የጠገቡ ሰራተኞች በየጠረዛቸዉ ተቀምጠዋል፤ በቢሮ ዉስጥ የሚገኘዉ የመጸሃፍ መደርደርያ ላይ የተቀመጡት መዝገቦችም አቧራ ለብሰዉ ይታያሉ።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ