1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሳዉዲ የተመለሱ ኢትዮጵያዉያን

ረቡዕ፣ ኅዳር 11 2006

የስዑድ አረቢያ መንግስት ያለ ሕጋዊ ፈቃድ በግዛቱ ይኖሩ የነበሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዉጭ ሀገር ዜጎች ፈቃዳቸዉን እንዲያስተካክሉ የሰጠዉ የምህረት ጊዜ ካለቀ በኋላ ባጠናከረችዉ አሰሳ በሺዎች የሚቆጠሩትን ወደየመጡበት መመለሱን ተያይዛዋለች።

https://p.dw.com/p/1ALVF
ምስል Reuters

ዘገባዎች እንደሚሉትም እስካሁን 60 ሺህ ያህሉን ሸኝታለች ፍተሻና ወደየሀገር መመለሱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነዉ የሀገር ዉስጥ ሚኒስትሩ ያመለከቱት። በተመሳሳይ ሁኔታ እዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁ ወደሀገር መመለስ መጀመራቸዉ ተሰምቷል። ዛሬም በሪያድና ሌሎች የሳዉዲ ግዛቶች ከዚያ የመዉጫ ቀናቸዉን እየጠበቁ፤ አደጋ ላይነንና ድረሱልን የሚሉት ወገኖች ቁጥራቸዉ ቀላል ባይሆንም። የኢትዮጵያ መንግስት ችግር ላይ ያሉት ዜጎች በቀጣይ ሳምንታት ዉስጥ ተጠቃለዉ ሊገቡ እንደሚችሉ ገልጿል። እስካሁንም ከአራት ሺህ በላይ ገብተዋል። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ወደሀገር ቤት መመለስ ከቻሉት አንዳንዶቹን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ