1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደደቢት እና ባህር ዳር

ቅዳሜ፣ ጥር 4 2011

ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ የተደረገበት የእግር ኳስ ግጥሚያ በደደቢት እና በባህር ዳር እግር ኳስ ቡድን መካከል ተካሂዷል። ይህንን ጨዋታ ለየት የሚያደርገው ከረዥም ጊዜ በኋላ በመካሄዱ ነው። እንደሚታወቀው በሁለቱ ክልሎች የሚገኙት የእግር ኳስ ክለቦች ደጋፊዎች መካከል ተፈጥረው በቆዩ አለመግባቶች ግጥሚያዎች ተቋርጠው ነበር።

https://p.dw.com/p/3BSeP
Äthiopien Fußballspiel in der Amhara Region
ምስል DW/A. Mekonnen

ደደቢት እና ባህር ዳር

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውስጥ ከሚጫወቱት የትግራይ ክልል ቡድኖች መካከል ከአመት በኋላ ደደቢት በአማራ ከልል ሜዳ ዛሬ መጫወት ጀመረ፡፡ ስፖረት የፖለቱካ ፍላጎት ማስፈፀሚያ እንዳልሆነ የአማራ ክልል መንግስት አስታውቋል፡፡
እንደሚታወቀው በሁለቱ ክልሎች የሚገኙት የእግር ኳስ ክለቦች ተፈጥረው በቆዩ አለመግባቶች ምክንያት ከአለፈው ህዳር 2010 ዓ.ም ጀምሮ በየሜዳቸው ጨዋታ አድርገው አያውቁም፡፡ በዚህም የሁለቱም እግር ኳስ ክለቦች ብዙ ጥቅሞችን አጥተው ቆይተዋል ሲሉ የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ያስረዳሉ፡፡
የሁለቱም ክልሎች የስፖርት ደጋፊዎች፣ አጠቃላይ ህዝቦችና አመራሩ ባደረጉት ጥረት ቡድኖች አንዱ በሌላው ሜዳ እንዲጫዎት ስምምነት ላይ በመድረሳቸው በቀዳሚው ሳምንት ሁለት የአማራ ክልል የሊግ ቡድኖች በአክሱምና በመቀሌ ከተሞች ስፖርታዊ ጨዋነት በተከተለ መልኩ ጨዋታቸውን አድርገው ተመልሰዋል፡፡
በትግራይ ክልል ከሚገኙ የፕሪምየር ሊግ ቡድኖች መካከል በአማራ ክልል ሜዳ ለመጫወትም ደደቢት የእግር ኳስ ቡደን በቀዳሚነት ባህር ዳር ገብቷል፡፡ 
የጨዋታውን ቅድመ ዝግጅትና የባህር ዳርን ቆየታ በተመለከተ ከደደቢት ተጫዋቾች መካከል -አብርሀም ታምራት ቆይታቸው ጥሩ እንደነበርና ህብረተሰቡ ስፖርትን ከፖለቲካ ሊለየው እንደሚገባ አመልክቷል ።
ስፖርት መዝናኛ እንጂ የፖለቲካ ፍላጎት መገለጫ አይደለም ያሉት አቶ አሰማኸኝ ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ነው የሚናገሩት፡፡ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ያልተለየው ይህ ጨዋታ በባህር ዳር 2 ለባዶ አሸናፊነት ተጠታቅቋል፡፡

Äthiopien Fußballspiel in der Amhara Region
ምስል DW/A. Mekonnen

ዓለምነው መኮንን
ልደት አበበ