1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጽሞና ቀናትና መገናኛ ብዙኃን 

ሐሙስ፣ ሰኔ 10 2013

በዚህም መሠረት ማኒፌስትቶዎችን ማስተዋወቅና ዕጩ ተወዳዳሪዎችንም ማነጋገርና መዘገብ የተከለከለ ነው። ይህ ማለት ግን ስለ ድምፅ አሰጣጥ፣ ስለ ምርጫ ሂደቱ፣ ስለ መራጮች ተስፋና ዝግጅት መራጮችንና ምርጫውን የተመለከተ ዘገባ አይሰራም ማለት እንዳልሆነ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3v7jJ
Logo | National Election Board of Ethiopia
ምስል National Election Board of Ethiopia

አራት የጥሞና ቀናት

ማንኛውም የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት አራት የጥሞና ቀናት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴዎችን መዘገብ እንደማይችል የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ዑደት መመሪያ አስቀምጧል።በዚህም መሠረት ማኒፌስትቶዎችን ማስተዋወቅና ዕጩ ተወዳዳሪዎችንም ማነጋገርና መዘገብ የተከለከለ ነው። ይህ ማለት ግን ስለ ድምፅ አሰጣጥ፣ ስለ ምርጫ ሂደቱ፣ ስለ መራጮች ተስፋና ዝግጅት መራጮችንና ምርጫውን የተመለከተ ዘገባ አይሰራም ማለት እንዳልሆነ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።መገናኛ ብዙኃኑ ይህንን መመሪያ እንዴት እየተገበሩት እንደሆን የሕትመትና የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃንን ጠይቀናል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዘገባ አጠናቅሯል
ሰሎሞን ሙጬ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ