1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦነግ የአመራሩን ውዝግብ ለመፍታት ጠቅላላ ጉባኤ 

ማክሰኞ፣ የካቲት 30 2013

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. አንስቶ ሲያወዛግበው የከረመውን የአመራር አለመግባባት እልባት ለመስጠት ጉባኤ ለማካኼድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዐስታወቀ።  የግንባሩ የአመራር ውዝግብ  እልባት የሚያገኘው በፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክረ-ሐሳብ አቅርቦ ነበር።

https://p.dw.com/p/3qP8M
 Logo Oromo Liberation Front

ጉባኤ ለማካኼድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዐስታውቋል

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. አንስቶ ሲያወዛግበው የከረመውን የአመራር አለመግባባት እልባት ለመስጠት ጉባኤ ለማካኼድ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጠ። 
የግንባሩ የአመራር ውዝግብ  እልባት የሚያገኘው በፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክረ-ሐሳብ አቅርቦ ነበር። የግንባሩ ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቴ ዑርጌሳ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ጉባኤውን የሚያመቻች ገለልተኛ ኮሚቴ ወደ እንቅስቃሴ መግባቱንና የመሥሪያ ቦታ ብቻ ፈተና ሆኖበት መዘግየቱን አንስተዋል።
ውዝግብ ውስጥ ከገቡት እና ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳን ሲከሱ ከነበሩት አመራር አንዱ የሆኑት አቶ ቀጄላ መርዳሳ ግን የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ እስካሁን የዘገየው በአመራሩ ፍላጎት ማጣት ነበር ይላሉ።

ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ