1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ዓርብ፣ የካቲት 24 2009

በትላንትናዉ እለት በአዳማ ከተማ የተጀመረዉ የጫፌ ኦሮሚያ አምስተኛ የስራ ዘመን፣ ሁለተኛ ዓመት፣ 5ኛ መደበኛ ጉባኤዉን ዛሬ እንደሚያጠናቅቀ ለመረዳት ተችለዋል።

https://p.dw.com/p/2YcKa
Äthiopien, Adama
ምስል DW/M. Yonas Bula

Chaffe Oromia on the Special Interest - MP3-Stereo

የጉባኤዉ ዋና አጄንዳ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነዉን የ 2009 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሰራ አፈፃጸም ሪፖርት ትላንት ለጫፌ አባላት ለግምገማ ቀርቦ እንደነበረ የጫፌ ኦሮሚያ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች አላፊ አቶ ሃብታሙ ደምሴ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ትላንት በስብሰባዉ ላይ ለተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርፅሰ መስተዳደር ለአቶ ለማ መገርሳ ከጨፌ አባላት ጥያቄዎች ተነስቶ እንደነበረም ተጠቁመዋል። ከጥያቄዎቹ መካከል አንዱ የሆነዉና በተደጋጋሚ ሲነሳና ስያከራክር የነበረዉ የኦሮምያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ያለዉን ልዩ ጥቅም እንዲከበር የሚለዉ ጥያቄ የት ደረሰ የሚል መሆኑም ተጠቅሰዋል። አቶ ለማ መገርሳ ጥያቄዉን ለፌዴራል መንግስት መላካቸዉንና መልስ እየተጠባበቁ እንደሆነ መናገራቸዉ ታዉቋል።

የጫፌ አባላት ያነሱት የኦሮሚያ ክልል ከአድስ አበባ ያለዉን ልዩ ጥቅም ጥያቄ አሁን ብቻ ሳይሆን በተለያዩ መድረኮች ሲነሱ እንደነበረ አቶ ሃብታሙ አስታዉሰዉ ርፅሰ መስተዳደሩ ጉዳዩ  በእርጋታ መታየት እንዳለበት መናገራቸዉ ተነግሮአል። አቶ ለማ መገርሳ ለፌዴራል ላቀረቡት  ጥያቄ መልስ የሚጠባበቁበትን የግዜ ገደብ አስቀምጠዋል? ተብሎ ስጠየቁ፣ «ከግዜ ገደብ ጋር በተገናኘ ያነሱት የለም። ዞሮ ዞሮ ግን ለፌዴራል የተላከዉን ጥያቄ መልስ እንቀበላለን ማለት ሳይሆን፣ ጥያቄዉ በጥናት ላይ የተመሰረተ መልስ እንደሚያገኝ ነዉ። ይህ ጥናት ደግሞ በተለያዩ መንገዶች መታየት አለበት፣ ለምሳሌ በፖለቲካና በሕግ በኩል፤ ህዝቡንም ሆነ ክልሉን በሚጠቅም መንገድ መታየት አለበት የሚል ነዉ። መቸኮል የለብንም፣ ጉዳዩ  በሰከነ መንፈስ መታየት አለበት  የሚል ነዉ፤ በአጠቃላይ መልሳቸዉ የነበረዉ።»

በ1987 ዓ.ም የፀደቀዉ የአገሪቱ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 49 ንዑስ አንቀስ አምስት ላይ ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ የመኅበራዊ አገልግሎት ማግኘት፣ የተፈጥሮ ኃብት መጠቀምና የጋራ አስተዳደር የመመስረት መብት እንደምታከበር ይጠቅሳል። ይሁን እንጅ እስካሁን ይህን ልዩ ጥቅም የሚያስከብር ዝርዝር ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዳለተዘገጀለትና ላለፉት አስርተ ዓመታት የክልሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ ችላ ማለቱን ባለሙያዎች ይተቻሉ። ይህም ባለመሆኑ ይላሉ ተችዎቹ ልዩ ጥቅሙን አስመልክቶ ጥያቄ ለሚያነሱት መታሰርና መሞት ምክንያት ሆኖዋል ብለዋል።

የጨፌን ስብሰባ አዳማ ሆኖ በቅርበት የሚከታተለዉ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ግለሰብ የከተማዋ ነዋሪ ግን ፣ የጫፌ አባላት እንድ አይነት ጥያቄ ማስነሳታቸዉ በጉባኤዉ ያልተለመዱ ናቸዉ ይላሉ። ይሁን እንጅ ርዕሰ መሰተዳደሩ አጥጋብ መልስ አለሰጡምም፣ ከፌዴራልም መንግስትም ቢሆን መልስ መገኘቱን ይጠራጠራሉ ሲሉ እኝህ የአዳማ ነዋቲ አክለዉ ተናግረዋል።

በጉባኤዉ ወቅት የጨፌ ኦሮሚያ አባላት የኦሮሚያ ክልል የግብር አስተዳደርን ለመወሰን የወጣዉን ረቂቅ አዋጅ ላይ እንደተወያዩና የጨፌ ኦሮሚያ አባላትን ሥነ-ስረዓት ለማሻሻል የወጣዉን ረቂቅ አዋጅ መወያየታቸዉና አዲስ ሹመቶች እንዳጽደቁ አቶ ኃብታሙ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ