1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

"እንነጋገር" - የአቤል ሙሉጌታ ሶስተኛ አልበም

እሑድ፣ ግንቦት 18 2011

 ወጣቱ ሙዚቀኛ አቤል ሙሉጌታ እንነጋገር የሚለውን 3ኛ የሙዚቃ አልበሙን ለሙዚቃ አድማጭ ቤተሰብ አበርክቷል፡፡ ተፈጥሮን የመረዳትና የማክበር እንዲሁም የማድነቅ ጉዳዮችን የዳሰሰበት ይህ አልበሙ ግጥምና ዜማውም የተሰራው በራሱ በአቤል ነው፡፡

https://p.dw.com/p/3J7s9
Äthiopien Abel Mulugeta
ምስል DW/S. Muchie

ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከDW ጋር

ወቅታዊ ጉዳዮችን እየዳሰሰ ሰው መነጋገር እንዳለበት፡ የሰው ልጅ ድንቅ ፍጥረት መሆኑን አምኖ ቢኖር ስስትና ራስ ወዳድነት ሊከስሙ እንደሚችሉ ያወሳል፡፡ ለስለስ ባለ የሙዜቃ ስልተ ምት የተቀናበረው እነጋገር ፍቅርን ምንድን ነህ እያለም ይጠይቃል፡፡ ሶስት ሙዚቃዎችም ስለዚሁ ጉዳይ አተኩረው ተሰናድተዋል፡፡ ችግረኞችን መጠየቅ ፡ ማየት ፡ ማህበራዊ ይሉኝታችንን እና የስነ ልቦናችንን የት ላይነትም ዘመን መስካሪ ሆኖ እንዲያወሳ በሙዚቃው ዳስሶበታል፡፡

አቤል በሱዳናኛ የሙዚቃ ስልተ ምትም ብቅ ብሏል፡፡ ወድቆ መነሳትም ለራስ ጥቅም ይሆናል እያለ ሰው ሁሌም በተስፋ የተሞላ ይሆን ዘንድ አስረግጦ ሃሳቡን በዜማ ለውሶ እንካችሁ ብሏል፡፡ስራው ከብዙ ወዳጆቹና አድናቂዎቹም ጥሩ ተቀባይነት እንዳገኘለት ፡ በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ የአልበም ምርቃት እንደሚያደርግና የሃገር ውስጥ እና ውጭ ኮንሰርቶችን ለማድረግ ከ ፕሮዱሰሮቹ ጋር ስምምነት ማድረጉንም ይናገራል፡፡

አቤል ወቅታዊ ጉዳይን ሲዳስስ ዛሬ ላይ ሆነን በትናንት ነገር መጋጨታችን የራስን ጊዜ ዋጋ ማሳጣት ነው ፡ ከአባቶቻችን ተምሮ በራስ ዘመን የሚገባን ሰርቶ ማለፍ ተገቢ ነው ይላል፡፡ሙዚቃ ማድመጥ የሚወደው አቤል ተወዳጅ ሙዚቀኛ ፊልም በተሌም የካርቱን ፊልም ከልቡ ይወዳል ፡፡ የንዋይ ደበበ የሙዚቃ ግጥም አጻጻፍ ስልት ይደንቀዋል፡፡ የቴዲ አፍሮ ግጥሞች እና የአገላለጽ መንገድ ይማርከዋል፡፡የቴዎድሮስ ታደሰ ፡ የአስቴር አወቀ ፡ የዘሪቱ ከበደ አድናቂ ነው፡፡ የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰን በድምጽ አወጣጥ ትንፋሹ ይማረክበታል፡፡የትዳር አጋሩን በሞት ያጣው አቤል አሁን ሁሉም ለምክንያት ነው በሚል ተጽናንቶ ከሙዚቃ ስራው በላይ መክሊት እና ማስተዋል የተባሉ ልጆቹንም እያሳደገ ይገኛል፡፡

ሰለሞን ሙጬ

ልደት አበበ