ኤቦላን ለመታገል ተፈላጊው ዓለም አቀፍ ትብብር፣
ሐሙስ፣ መስከረም 29 2007ማስታወቂያ
በምዕራብ አፍሪቃ ቢያንስ የ 3,800 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን አደገኛ በሽታ ለመታገል የሀኪሞች ርዳታ ፤ ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችና መሠረታዊ ሰባአዊ ርዳታ ምግብ ጭምር አስፈላጊ መሆኑ ተገለጠ። ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የሚጠበቀው ርዳታ የ 300 ሚሊዮን ዶላር እጥረት እንደታየበት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የገለጠ ሲሆን፤ የዓለም ባንክ፣ ኤቦላ ፣ እስከመጪው 2015 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ከቀጠለ የ 32 ,6 ቢሊዮን ዶላር ኪሣራ እንደሚያስከትል አስጠንቅቋል። አሜሪካዊው የኢቦላ ሕመማተኛ ትናንት ካረፈ ወዲህ ምን ዓይነት ስሜት ፈጥሮ ይሆን ? የዋሽንግተን ዲ ሲውን ዘጋቢአችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬው ነበር።
አበበ ፈለቀ
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሠ