ኤቦላን ለመቆጣጠር የአዉሮጳ ባለስልጣናት ያቀረቡት ሃሳብ
ረቡዕ፣ ኅዳር 10 2007ማስታወቂያ
በዋናነት የሰብዓዊ ርዳታ ኮሚሽነር እና የኅብረቱ የኤቦላ እርዳታ አስተባባሪ ዶክተር ክሪስቶስ ስታላይንደስ፤ የጤና ኮሚሽነሩ ቬልተኒስ አንድሩካይቲስ የሚገኙበት ቡድን ከሕዳር 3 እስከ 7 በላይቤሪያ፣ ጊኒና ሴራሊዮን በመዘዋወር የበሽታዉን ስርጭት ሁኔታ እና ስርጭቱን ለመከላከል እየተደረጉ ያሉትን ጥረቶችና ችግሮች ገምግሟል። የጉብኝቱንም ግኝቶች በዓለም ዓቀፉ ኅብረተሰብና በተለይም በአዉሮጳ ኅብረት በኩል ባስቸኳይ ሊደረጉ ይገባል ያሏቸዉን ዶክተር ክሪስቶስ ስታላይንደስ ለአዉሮጳ ፓርላማና ለኅብረቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለየብቻ በዝርዝር አቅርበዋል። ትናንትናም ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ