1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራዊዉ ጋዜጠኛና የአፍሪቃ ኅብረት

ሰኞ፣ መጋቢት 9 2005

የስዊድን ዜጋ የሆነዉ ትዉልደ ኤርትራዊዉ ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅ ጉዳይ በአፍሪቃ ኮሚሽን የህዝቦች የሰብዓዊ መብት አስከባሪ በኩል የሚጠና መሆኑ ተገለፀ።

https://p.dw.com/p/17zjf

ጋዜጠኛዉ ኤርትራ ዉስጥ ከታሰረ 12ዓመታትን እንዳስቆጠረ ፅህፈት ቤቱ ፓሪስ የሚገኘዉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች RSF አመልክቷል። የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ለጋዜጠኛዉ ጉዳይ ትኩረት መስጠቱንም RSF አበረታች ሲል ከሰሞኑ ባለወጣዉ መግለጫ ጠቅሷል። ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የRDSFን መግለጫ መሠረት በማድረግ የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት እና የሰብዓዊ መብት ባለሙያ ሳላህ ሃማድ በኮሚሽኑ በኩል እየተደረገ ስላለዉ ጥረት በማነጋገር ተከታዩን ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ