1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራዉያን ስደተኞች ወደጣሊያን መላካቸዉ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 10 2006

ጀርመን ኤርትራዉያን ተገን ጠያቂዎችን ወደጣሊያን መመለስ መጀመሯ እያነጋገረ ነዉ። ዛሬ ጠዋት የጀርመን ፖሊሶች ሶስት ኤርትራዉያንን ወደጣሊያን ልከዋል።

https://p.dw.com/p/1CKKN
Italien Flüchtlingsdrama Lampedusa Flüchtlingsboot
ምስል picture-alliance/ROPI

መንግስትም ሆነ ፖሊስ ተገን ጠያቂዎቹ ወደጣሊያን እንዲላኩ የተደረገዉ በመጀመሪያ ወደአዉሮጳ ሲገቡ እግራቸዉ የረገጠዉ ሀገር በመሆን ጥገኝነቱን እንዲጠይቁ የሚለዉን የጋራ መግባቢያ በመጥቀስ አመልክተዋል። ለስደተኞች የሚቆረቆሩ ድርጅቶች በበኩላቸዉ በአሁኑ ወቅት በየዕለቱ ከመቶና ሺዎች የሚገመቱ ስደተኞች የሚገቡባት ጣሊያን ለእነሱ አስፈላጊ መሠረታዊ ነገሮችን የማቅረብ አቅም እንዳጠራት ያስረዳሉ። በጀርመን ምንም ሰዉ ስደተኛ አይደለም የተሰኘዉ መንግስታዊ ያልሆነ ለስደተኞች የሚቆረቆር ድርጅት ወኪልን በጉዳዩ ላይ ያነጋገረዉ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል አጭር ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ