ኢትዮ-ቴሌኮም የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 16 2011ማስታወቂያ
ኢትዮ-ቴሌኮም የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በሃገሪቱ በተከሰተው የኢንተርኔት መረብ መቆራረጥ ድርጅቱ ብዙ ሚሊዮን ብር ማጣቱን ገልጸዋል። ሆኖም ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ ከ 40 እስከ 50 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ አድርጎም ጭምር 36,3 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱ በመግለጫው ተጠቅሷል። የፋይበር መስመር መቆራረጥ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር እና የኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ኢትዮ ቴሌኮምን በበጀት ዓመቱ ውስጥ ያጋጠሙት ዋነኛ ተግዳሮቶች እንደሆኑም ተጠቁሟል። ከዶይቼ ቬለ «DW» ለቀረበላቸው ጥያቄ አጭር ምላሽ የሰጡት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ-ቴሌኮም ከዉጭ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት ለመስራት ያለበትን ችግር አብራርተዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የታደመው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
ተስፋለም ወልደየስ