1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮ ቴሌኮም በትግራይ ያጋጠመው ችግር

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 1 2013

በሰሜን ኢትዮጵያ መቀሌ እና ሽሬ ዋና ጣቢያዎች ላይ የሚገኙት የቴሌኮም የመገናኛ መስመሮች ሙሉ በሙሉ ሆን ብሎ በማቋረጥ የኃይል አቅርቦትና ማሰራጫዎች እንዲስተጓጎሉ መደረጉን ኢትዮ ቴሌኮም ተናገረ።

https://p.dw.com/p/3mXQ2
Äthiopien Addis Abeba | Ethio Telecom building
ምስል DW/H. Melesse

«አገልግሎቱ የሚስተካከልበት ጊዜ አልተገለጸም»

በሰሜን ኢትዮጵያ መቀሌ እና ሽሬ ዋና ጣቢያዎች ላይ የሚገኙት የቴሌኮም የመገናኛ መስመሮች ሙሉ በሙሉ ሆን ብሎ በማቋረጥ የኃይል አቅርቦትና ማሰራጫዎች እንዲስተጓጎሉ መደረጉን ኢትዮ ቴሌኮም ተናገረ። ድርጅቱ የመቀሌው ዋና ጣቢያ ላይ የትግራይ ልዩ ኃይል መለዮ የለበሱ ታጣቂዎችና ጭምብል ያጠለቁ ሰዎች በሌሊት እርምጃ ሲወስዱበት የሚያሳይ በደኅንነት ካሜራ የተቀረፀ ፊልም እንደደረውም ገልጿል። ኢትዮ ቴሌኮም የመንግሥት ፣ የፋይናንስና የትምህርት ተቋማትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ የደኅንነት ጥቃት ተሰንዝሮበት እንደነበርም ገልጿል። በቀጣይ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን በትግራይ የቴሌኮም አገልግሎት ወደመስጠቱ እንደሚገባ ያሳወቀው ተቋሙ መች እንደሚጀምር ግን አሁን መግለፅ እንደማይችልም አመልክቷል። 

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ