1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ግብፅ አባይ ግድብ ላይ የሰጠችዉን ሃሳብ ዉድቅ ማድረግዋን ገለፀች

ረቡዕ፣ መስከረም 7 2012

የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ በወቅታዊ የአባይ ግድብ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ የግድቡ ሁለቱ ተርባይኖች  ታህሳስ 2013 ሃይል የማመንጨት ስራ እንደሚጀምሩ አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/3Pocl
Äthiopien | Dr.eng. Sileshi Bekele
ምስል DW/S. Muchie

40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውኃ በየዓመቱ ይልቀቅ የሚለው ሃሳባቸው የሚሆን ነገር አይደለም

የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ በወቅታዊ የአባይ ግድብ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ የግድቡ ሁለቱ ተርባይኖች  ታህሳስ 2013 ሃይል የማመንጨት ስራ እንደሚጀምሩ አመልክተዋል። እሁድ እለት በነበረን የውኃ ሚኒስትሮች ድርድር በግብጽ በኩል የቀረበው የህዳሴው ግድብ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውኃ በየዓመቱ ይልቀቅ የሚለው ሃሳባቸው የሚሆን ነገር አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአስዋን ግድብ 165 ሜትር ከፍታ ላይ ሆኖ እንዲቀጥል እንሻለን የሚለው ጥያቄያቸውም ተቀባይነት የሌለውና የማያስኬድ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ህዳሴው ግድብ ላይ የግብጽ ባለሙያዎች ይኑሩ የሚለው ፍላጎታቸው  የሃገራችንን ሉአላዊነት የሚጋፋ በመሆኑ የማንቀበለው ነው ብለዋል። የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ስለ ግድቡ ያላቸው የዘገባ እና የመረጃ ስርጭትም ፍትሃዊ እንዳልሆነና  የእኛዎችም ተገቢ መረጃ በማሰራጨት የሃገርን ጥቅም የማስጠበቅ ተግባር ፈጽሙ በማለት ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ ግብጽ ላቀረበችው ፕሮፖዛል አንድ ሃገር ብቻውን መሰል ጥያቄ ማቅረብ ስለማይችል እኛም ሱዳንም የአጸፋ ፕሮፖዛል አዘጋጅተን በተቋቋመው የ3ቱ ሃገሮች ብሔራዊ ገለልተኛ የሳይንስና ምርምር ኮሚቴ መስከረም 19 -20 ይደራደሩበታል ብለዋል። ሃገራዊ አንድነታችንን በማስጠብቅ የውስጥ ችግራችንን ያዩ ሁሉ መጠቀሚያ እንዳያደርጉን ሲሉም ጠይቀዋል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ