1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፣ የ 2007 ምኞትና ተስፋ

እሑድ፣ መስከረም 11 2007

ባለፈው ሳምንት እሑድ በክፍል አንድ ውይይታችን ፣ የገባውን አዲሱን ዘመን 2007 ዓ ም ን መንስዔ በማድረግ፤ በኢትዮጵያ ፣ ከገሐዳዊው ይዞታ ጋር ምኞትና ተስፋ እንዴትና ምን ቢደረግ እውን ሊሆኑ እንደሚችሉ 3 ቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን ፣ ከአዲስ ዓመት

https://p.dw.com/p/1DG0Y
ምስል DW

ትዝታ ሌላ ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ የአብሮነት ስሜት ፤ መቻቻል፤ የባህል መወራረስ፣ ለዘመናዊ አስተዳደር ጠቃሚ በሆኑ ባህላዊ እሴቶች ላይ ሐሳባቸውን አካፍለውን እንደነበረ ይታወስ ይሆናል። በዛሬው በሁለተኛውና የመጨረሻ ክፍል ውይይታችን ትምህርት፣ ምርምርና ወጣቶች፣ እንዲሁም ዘንድሮ የሚካሄደው ምርጫና ፣ እንዴት ቢሠራ ስለሚሰምርበት ሁኔታ ተወስቷል።

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በአመዛኙ የወጣቶች ሀገር ናት ። በ 10ና በ 24 ዓመት የዕድሜ ዕርከን ላይ የሚገኘው እንኳ 30,5 ሚሊዮን ገደማ መሆኑ ነው የሚነገረው። 35 ከመቶ መሆኑ ነው። ዕድሜው ከ 40 ዓመት በታች የሆነውን ትውልድ ከጨመርን ደግሞ ፣ መጠኑ የትና የት ነው! ታዲያ ይኸው ወጣት ትውልድ አገር ገንቢ ዜጋ መሆን የሚችለው በምን ዓይነት ትምህርት ቢታነጽ ነው?

ተክሌ የኋላ

አዜብ ታደሰ