ኢትዮጵያ ዉስጥ የታሰሩት የስዊድን ጋዜጠኞች አቋም
ረቡዕ፣ ጥር 2 2004ማስታወቂያ
በየመጀመሪያ ስማቸዉ ስማቸዉ ማርቲንና ጆን ተብለዉ የሚጠሩት የጋዜጠኞችን መግለጫ የጠቀሰዉ የሲዊድን ዜና አገልግሎት እንደዘገበዉ ጋዜጠኞቹ «ኢትዮጵያ ዉስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየ» ያሉትን ይቅርታና ምሕረት ለመጠቀም ወስነዋል።ከጋዜጠኞቹ ጠበቆች አንዱ አቶ ደርበዉ ተመስገን እንዳሉት ግን ሥለ ደንበኞቻቸዉ ዉሳኔ የሚያዉቁት ነገር የለም። ጠበቃና የሕግ አማካሪ ደርበዉ ተመስገንን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሀመድ
አርያም ተክሌ