1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፤ ተቃዋሚዎቹ ተፈቱ

ማክሰኞ፣ የካቲት 8 2008

የአምስቱ ፖለቲከኞች ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን እንዳስታወቁት የደንበኞቻቸዉን ክስ ይመለከት የነበረዉ የሐገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለቱ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ የወሰነዉ ባለፈዉ አርብ ነበር።ይሁንና ፖለቲከኞቹን ያሠረዉ ወሕኒ ቤት የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ ለማክበር ሲያቅማማ ቆይቶ ዛሬ ጠዋት አሰናብቷቸዋል

https://p.dw.com/p/1HwJJ
ምስል AP

[No title]

በአሸባሪነት ወንጀል ከተከሠሱ አምስት የኢትዮጵያ መንግሥት የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች መካከል አቶ ሐብታሙ አያሌዉ እና አቶ አብረሐም ሠለሞን ዛሬ በነፃ ተለቀቁ።የአምስቱ ፖለቲከኞች ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን እንዳስታወቁት የደንበኞቻቸዉን ክስ ይመለከት የነበረዉ የሐገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለቱ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ የወሰነዉ ባለፈዉ አርብ ነበር።ይሁንና ፖለቲከኞቹን ያሠረዉ ወሕኒ ቤት የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ ለማክበር ሲያቅማማ ቆይቶ ዛሬ ጠዋት አሰናብቷቸዋል።የተቀሩት ሰወስቱ ፖለቲከኞች ግን ፍርድ ቤትን በመድፈር ወንጀል ሥለተፈረደባቸዉ አልተለቀቁም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጠበቃ አመሐን አነጋግሯቸዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ