1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በቱኒሲያ፤

ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2005

የሊቢያው ጦርነት ከመካሄዱ በፊትና በጦርነቱ ወቅት ፤ ከዚያም በኋላ ፣ ወደ ሌሎች ሀገራት ፤ በተለይም ወደ አውሮፓ ለመግባት የሜድትራንያንን ባህር በጀልባዎች ለማቋረጥ ሲሞክሩ ፤ ዘግናኝ ሁኔታ እያጋጠማቸው በመስመጥ ህይወታቸውን ስላጡ ኢትዮጵያውያን

https://p.dw.com/p/16jL4
ምስል AHMED OUOBA/AFP/GettyImages

ሶማሌዎች ኤርትራውያንና ሌሎችም የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ባለፉት 2 ዓመታት ገደማ በተደጋጋሚ ዘገባዎችን አዳምጠናል። የከፊሉ ስደተኞቹ እንጂ የብዙዎቹ ችግር እስከዛሬ

እልባት እንዳላገኘ ይሰማል። ከሊቢያው ጦርነት ሸሽተው ቱኒሲያ የገቡ ኢትዮጵያውያን እስካሁን በዚያው ድንበር አካባቢ  የሚገኙ ሲሆን፤ ትናንት አደባባይ በመውጣት ለ UNHCR ስለወደፊቱ ዕጣቸው አቤት ብለው ነበር። ተክሌ የኋላ ስልክ በመደወል ስደተኞቹን አነጋግሮ ነበር።

02.09.2012 online Karten Libyen Bengasi arab

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት AI ሊቢያ ውስጥ፤ በጥቁር አፍሪቃውያን ላይ የሚካሄደው ቁም ስቅል ማሳያ የግፍ እርምጃና  አፈሳ  ተባብሶ መቀጠሉን አጋልጧል። ካለፈው ዓመት ግንቦት እስካለፈው መስከረም፤ በሊቢያ 9 የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን የጎበኙት የ AI ሰዎች፤ 2,700 ያህል የውጭ ተወላጆች፤ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ነው የገባችሁ ተብለው በእሥር በመማቀቅ ላይ መሆናቸውን ተገንዝበዋል። ከፊሉ የሊቢያ ህዝብ ፣ የሌሎች አገሮች ተወላጆች የሆኑ ጥቁር አፍሪቃውያንን  የጋዳፊ ቅጥረኛ ወታደሮች ነበራችሁ እያሉ እንደሚያጥላሏቸው ነው AI ያስታወቀው።

E-Learning
ምስል GIZ/Ina Zeuch

ስለሚያጋጥም  ስንትና ስንት አሰቃቂ ፈተና ፤ መከራ እየሰሙም ቢሆን፤  ወደ ደቡብ ፣ ሰሜንና ምሥራቅ የሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን መጠን ሊገታ አልቻለም። የስደታቸው ምክንያት ዘርፈ ብዙ ነው። ሊቢያ ከገቡ በኋላ በጦርነቱ ሳቢያ ሊቢያና ቱኒሲያ ድንበር አካባቢ ፣ ቱኒሲያ ግዛት ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዚያ የሚገኙ ሲሆን፣ ትናንት አደባባይ ስለወጡበት ምክንያት ጥቂቶቹን አነጋግሬ ነበረ። በመጀመሪያ አንዲት ወይዘሮ እንዲህ ብለውናል።

ሌላ ጎልማሣም  እንዲህ ብሶታቸውን አሰምተዋል ፤ አብረዋቸው ከነበሩት አንደኛው ተርጎሞልናል።

ቴዎድሮስ የተባለው ፤ ችግሩን መገናኛ ብዙኀን አውቀው ለሚመለከታቸው ጭምር በማሳሰብ መፍትኄ እንዲያፈላልጉን በማለት እንዲህ ነበረ የገለጸልን።

Symbolbild afrikanische Flüchtlinge im Mittelmeer
ምስል picture-alliance/Milestone Media

በዚያው በቲኒሲያ የሚገኙትን፤ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቅርንጫፍ  መ/ቤት ባለሥልጣናት አግኝተን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ አልተሣካልንም።

ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሰደዱ የሚያጋጥማቸው አሰቃቂ አደጋ ብቻ ሳይሆን ፣ የመሰደዳቸው ምክንያትና  ፤ መፍትኄው፣ በሀገር ውስጥም በውጭም ያለውን ኢትዮጵያዊውን ማኅበረሰብ በጥሞና  ሊያነጋግር የሚገባ ጉዳይ ነው።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ