1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዊዉ ሳይንቲስት የዓለም ሎሬት ተባሉ

ሰኞ፣ ሰኔ 8 2001

በአሜሪካን አገር የፖርዱ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊዉ የእርሻ ምሁር የዘንድሮዉ የዓለም የምግብ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

https://p.dw.com/p/IAEA

ኢትዮጵያዊዉ ሳይንቲስት ዶክተር ገቢሳ ኢጄታ ለሽልማት የበቁት ድርቅና በሽታ የማያጠቃዉ የማሽላ ዘር ባደረጉት ምርምር መፍጠር በመቻላቸዉ ነዉ። ዶክተር ገቢሳ በዚህ ጥረትና ዉጤታቸዉ የዓለም ሎሬት የሚል የክብር ማዕረግና ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ። የዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ተሸላሚዉን ኢንትዮጵያዊ ሳይንቲስት አነጋግሯል።

አበበ ፈለቀ/ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ