1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በዚምባቡዌ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 20 2006

በዚምባቡዌ አቋርጠዉ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመሻገር የሞኮሩ 38 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች የዚምባቡዌን ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘዉ በመታሰራቸዉ ለከፋ ችግር መጋለጣቸዉ ተነገረ።

https://p.dw.com/p/1A9E4
epa03809922 Zimbabweans check election results posted outside a polling station in Mbare, Harare, Zimbabwe, 01 August 2013. Prime Minister Morgan Tsvangirai on 01 August declared Zimbabwe's general election to be 'null and void' due to allegations of vote rigging and warned the country was on the brink of a crisis. The country's most important independent network of election observers announced it too doubted the legitimacy of the ballot. The 89-year-old Zimbabwean president, Robert Mugabe, who has been at the helm of the country since 1980, has vowed to step down if he is declared the loser in the election. EPA/AARON UFUMELI
ምስል picture-alliance/dpa

ስደተኞች የተያዙት ከሞዛምቢክ ወደዚምባቡዌ ተሻግረዉ፥ ከዚምባቡዌ በአዉቶቡስ ወደደቡብ አፍሪቃ ሲጓዙ ነበር። የዚምባቡዌ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ኢትዮጵያዉያኑ ስደተኞች ከተያዙበት ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ባይትስብሪጅ በተባለዉ መቆጣጠሪያ ኬላ ላይ እንደታሠሩ ነዉ። በሐራሬ- ዚምባቡዌ የዶቸ ቬለ ወኪል ኮሎምቦ ስማቭሁንጋ እንደሚለዉ ስደተኞቹ ምግብ የሚያቀብላቸዉ ካላገኙ በረሐብ ይጎዳሉ።

በዚምባብዌ ፖሊስ መግለጫ መሰረት እነዚ እድሜያቸው በ20 እና30 መካከልየሚገኙ 38 ኢትዮጵያውያን በሞዛምቢክ በኩል ኣድርገው ነው የዛሬ ሳምንት ወደዚምባብዌ የዘለቁት። በህገወጥ መተላለፊያዎች በኩል። የተያዙትም ቢሆን ከምስራቃዊትዋ የዚምባብዌ ከተማ ከሙታሬ ኣውቶቡስ ተሳፍረው በባይትብሪጅ የማቐረጫ ኬላ በኩል ወደደቡብ ኣፍሪካለ መሻገር ሲሞክሩ ነው ተብለዋል። የባይትብሪጅ ኬላ ጠባቂ ፖሊሶች ኣዛዥ እንደሚሉት እነዚህ ስደተኞች በእሳቸው ኣጠራር ህገወጥ ፈላሾች በህገወጥ መንገድ ወደኣገሪቱ በመግባታቸው ምርመራ እየተካሄደቸው ይገኛል። በዚሁ ወንጀልም ክስ ይጠብቃቸዋል። ከእነዚህ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪም በተመሳሳይ ሁኔታ ወደኣገሪቱ የገቡ በርካታ ስደተኞች ኣሉ። የሁሉም ጉዳይ በኣገሪቱ ህግ መሰረት ይዳኛል ይላሉ የባይትብሪጅ ፖሊስ ኣዛዥ ላውሬን ሴቪንሄንጎ የዚህን ኣይነት ወንጀል ለማጣራት የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም የሚሉት ላውሬንሴ እነዚህን ስደተኞች ኣሳፍሮ ድንበር ለማሻገር ሲጘዝ የተገኘው ኣውቶቡስ ደግሞ ንብረትነቱ የፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ዛኑ PF ፓርቲ ሁነኛ አባል መሆኑም ሌላው ቅሌት ነው ሲሉም ኣክለዋል።

Zimbabwe's President Robert Mugabe addresses the crowd gathered to commemorate Heroes Day in Harare August 12, 2013. Mugabe told critics of his disputed re-election to "go hang" on Monday, dismissing his rivals as "Western-sponsored stooges" at a liberation war commemoration that was boycotted by his principal challenger. The Movement for Democratic Change (MDC) of Mugabe's rival Morgan Tsvangirai filed a court challenge on Friday against the announced landslide win of Mugabe and his ZANU-PF party in the July 31 vote, alleging widespread rigging and intimidation. REUTERS/Philimon Bulawayo (ZIMBABWE - Tags: POLITICS ELECTIONS HEADSHOT)
ምስል Reuters

ንብረትነቱ የም/ቤት እንደራሴ በሆነ ኣውቶቡስ 38 ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሳፈራቸውን በመረጃ ስናረጋግጥ ለመያዝ ኣላመነታንም ያሉት እኚሁ የፖሊስ ኣዛዥ የኢሚግሬሺን ባልደረቦችም ለዚሁ መተባበራቸውን ኣመስግነዋል። ባለስልጣናት ኣውቶቡሶችን ለህገወጥ ስደት እስከማመቻቸት ሲደርሱ ለመታገስ ኣይቻለንም ሲሉም ኣዛዡ ተናግረዋል።

በዚምባብዌ ኃራሬ የሚገኘው የዶቸ ቬሌ ባልደረባ ኮሎምበስ ማብሁንጋ እንደሚለው ደግሞ የእነዚህ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በእርግጥ ለውሳኔ ማስቸገሩ ኣይቀርም። ምክኒያቱም በዚምባብዌ ህግ መሰረት ያለፈቃድ የገባማንኛውም ስደተኛ ተይዞ ወደኣገሩ እንዲመለስ ነው የሚደረገው። ኣሁን ግን ዚምባብዌ ይህንን ለማድረግ ኣቅሙም የላትም።

ኮሎምበስ እንደሚለው በርካታ ስደተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሩዋንዳ፣ ኤርትራ እና ኮንጎ እየመጡ ወደደቡብ ኣፍሪካ ይሻገራሉ። ድንበር ላይ ሲያዙ ግን የማጎሪያ ካምፑ ይዞታ ኣሁን ኢትዮጵያውያኑ የሚገኙበት ማለት ነው በጣም ኣስቸጋሪ ነው። ስንቅ የሚያቀብል ዘመድ ከሌላቸው በተለይ ለምግብም ሊቸገሩ ይችላሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ ኮሎምበስ እንደሚለው ኃራሬ የሚገኙት የኣፍሪካ ኣገሮች ኢምባሲዎች ደግሞ ለዜጎቻቸው ደንታ ያላቸው ኣይመሉም።

ዚምባብዌ ከደቡብ ኣፍሪካ ጋር ባላት ቀጥተኛ ድንበር የተነሳ በኣፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ወደሆነችው ደቡብ ኣፍሪካ የበርካታ ኣገሮች ስደተኞች መሸጋገሪያ ሆና መቆየትዋ ይታወቃል። ሶስት ሚሊየን ያህል የራስዋ የዚምባብዌ ዜጎችም በደቡብ ኣፍሪካ እንደሚገኙ ሲታወቅ አብዛኞቹ ደግሞ በህገወጥ መንገድ የገቡ ናቸው። በየዓመቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደዚምባብዌ እንዲመለሱ ቢደረጉም ወዲያውኑ ግን በሌላ አቅጣጫ ተመልሰው እዚያው ደቡብ ኣፍሪካ ይገባሉ ተብለዋል።

ጃፈርአሊ

ነጋሽመሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ