ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች በታንዛንያ
ሐሙስ፣ ጥር 19 2008ማስታወቂያ
ባለፈዉ ሳምንት የሃገሪቱ ፖሊሶች አሸጋጋሪ ደላሎች ዳሬ ኤስ ሳላም ዉስጥ ሁለት ትናንሽ ክፍሎች ባሏት አነስተኛ ቤት ያጨቋቸዉ ከ40 በላይ ኢትዮጵያዉንን መያዛቸዉ መሰማቱ ይታወቃል። ከዚያ በፊት በርካታ ኢትዮጵያዉያን በከባድ መኪና ተጭነዉ ከታንዛኒያ ወደ ማላዊ ሊሻገሩ ሲሞክሩ በታንዛኒያ ፀጥታ አስከባሪዎች ተይዘዉ እንደነበርም ይታወሳል። የታንዛኒያ የሃገር ግዛት ሚንስትር ቻርልስ ኪትዋንጋ እንዳሉት መንግሥታቸዉ በሕገ-ወጥ መንገድ ታንዛኒያ የገቡ የዉጪ ሃገር ዜጎችን በተለይ ኢትዮጵያዉያንን ለመያዝና ወደ ሃገራቸዉ ለማጋዝ ልዩ ዘመቻ ጀምሯል። ታንዛኒያ ዉስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን በሕገ-ወጥ መንገድ ይኖራሉ ወይም ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመጓዝ ጊዜና ገንዘብ ይጠብቃሉ። ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ሃገር ታንዛንያ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለሚሰደዱ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ዜጎች ዋና መሸጋጋሪያ መሆንዋ ይታወቃል። ሥለ ሕገ-ወጥ የሰዉ አዘዋዋሪዎችና ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በተመለከተ የኬንያዉን ወኪላችንን አነጋግረነዋል።
ፋሲል ግርማ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ