1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ተዘጉ

ማክሰኞ፣ መስከረም 6 2012

ሁለቱን ሐገራት በኢትዮጵያ ሞያሌ በኩል የሚያገናኙት መጋቢ መንገዶች ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ መዘጋታቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ቢያስታዉቁም፣በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን መንገዶቹ አልተዘጉም ይላል

https://p.dw.com/p/3Pjh3
Wegweiser Autobahnschild Äthiopien
ምስል DW

ኢትዮ-ኬንያ መንገድ መዘጋት ምክንያቱና ችግሩ

የኬንያ መንግስት ሐገሩን ከኢትዮጵያ ጋር በሁለት አቅጣጫ የሚያገናኙ መጋቢ መንገዶችን መዝጋቱን የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎችና የኬንያ ባለስልጣናት አስታወቁ።የኬንያ መንግስት መንገዶቹን የዘጋዉ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር በርካታ ሕገ-ወጥ ጦር መሳሪዎች ከተያዙ በኋላ ነዉ።ሁለቱን ሐገራት በኢትዮጵያ ሞያሌ በኩል የሚያገናኙት መጋቢ መንገዶች ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ መዘጋታቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ቢያስታዉቁም፣በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን መንገዶቹ አልተዘጉም ይላል።አንድ የኬንያ ባለስልጣን ግን መንገዶቹ በኢትዮጵያና በኬንያ መንግስታት ስምምነት መዘጋታቸዉን አጋልጠዋል።የሐዋሳዉ ወኪላችን ሸዋን ግዛዉ ወጋየሁ ያነጋገራቸዉ የሞያሌ ነዋሪዎች እንደሚሉት መንገዶቹ በመዘጋታቸዉ የትራንስፖርትና የህዝብ ዝዉዉር ተስተጓጉላል።የአነስተኛ ንግድ ልዉዉጥም ቆሟል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ