1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮዽያ የተወሰኑ የሰብል ምርቶች ለውጭ ገበያ እንዳይቀርቡ የጣለችውን እገዳ አነሳች

ሐሙስ፣ ሐምሌ 8 2002

እገዳው የተነሳው በበቆሎና በማሽላ ምርቶች ላይ ብቻ ነው። ከሀገር ውስጥ የገበያ ፍላጎት በላይ በመሆኑ እገዳው እንደተነሳ መንግስት አስታውቋል። የዓለም የምግብ ድርጅት እርምጃውን አወድሶታል።

https://p.dw.com/p/OML4
እገዳው ከተነሳላቸው አንዱ ማሽላ ነውምስል Helge Bendl

ኢትዮዽያ የሰብል ምርቶች ለውጭ ገበያ እንዳይቀርቡ እገዳ የጣለችው ከሦስት ዓመት በፊት ነበር። በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ አማከለ ይማም እንደገለጹት በተለይ በሁለት ምርቶች ላይ እገዳው ተነስቷል። ምክንያቱም የተትረፈረፈ ምርት በመገኘቱ--እንደአቶ አማከለ ገለጻ። ለጊዜው እገዳው የተነሳው ለበቆሎና ለማሽላ ምርቶች ሲሆን በተቀሩት ላይ ግ ይቀጥላል። የዓለም የምግብ ድርጅት የእገዳው መነሳት ጠቃሚ እንደሆነ ጠቅሶ በቀጣይ ከ120 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ከኢትዮዽያ ገበሬዎች እንደሚገዛ አስታውቋል። ኢትዮዽያ ለውጭ ገበያ ምርቷን ለሽያጭ እንደምታቀርብ እየገለጸች ባለችበት በአሁኑ ጊዜ ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰው አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የቅድመ ረሀብ ማስጠንቀቂያ ዓለም ዓቀፍ ኔትወርክ ይፋ አድርጓል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ