1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢራን ከምርጫ ዉዝግቡ ማግሥት

ሰኞ፣ ሰኔ 22 2001

በኢራን ሰኔ 5 2001ዓ,ም የተካሄደዉ ምርጫ ዉጤት ከድምፁ አስር በመቶ የሚሆነዉ ዳግም እንዲቆጠር መንግስት አዝዞ መጀመሩን የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/Idc5
በኢራን ለሞቱ መታሰቢያ በበርሊንምስል AP

ምርጫዉ መጭበርበሩን በአጽንዖት የሚገልፁት ተቃዋሚ ፕሬዝደንታዊ እጩ ሚርሆሴን ሙሳቪ ዳግም ቆጠራዉን በማጣጣል ምርጫዉ እንዲደገም ጠይቀዋል። በሌላ በኩል የኢራን መንግስት የምርጫ ዉጤቱን ተከትሎ የተነሳዉን ተቃዉሞ አባብሰዋል ሲል ካሰራቸዉ ዘጠኝ የብሪታንያ ኤምባሲ ሰራተኞች መራከል አምስቱን መልቀቁን አስታዉቋል።

ሸዋዬ ለገሠ/ተክሌ የኋላ