1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢራን እና የእሥራኤል ዛቻ

ረቡዕ፣ መስከረም 22 2006

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት በኒው ዮርክ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ንግግር አሰምተዋል። ንግግራቸው በተለይ በኢራን እና በኑክልየር መርሀግብር ላይ ያነጣጠረ ነበር።

https://p.dw.com/p/19syj
ምስል Reuters

ኔታንያሁ ቀደም ሲልም በዋሽንግተን ከዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ጋ ባደረጉት ውይይት ላይ ዩኤስ በዚችው ሀገር ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንድታጠናክር ጠይቀዋል። ዩኤስ እና እሥራኤል ኢራን መርሀግብርዋን ምናልባት ለአቶም ጦር መሣሪያ ምርት ልትጠቀምብት እንደምትችል ነው በተደጋጋሚ የሚያስጠነቅቁት። ግን አዲሱ የኢራን ፕሬዚደንት ሀሳን ሮሀኒ ሀገራቸው የኑክልየር መርሀግብርዋን ለሰላማዊ ጠቀሜታ እንጂ የኑክልየር ጦር መሣሪያ ምርት እንደማታውለው እና በዚሁ ሰበብ ከምዕራቡ ጋ ለተፈጠረው ውዝግብ መፍትሔ ለማፈላለግ ዝግጁ አነደሆነች ሲገልጹ ተሰምቶዋል። ይኸው የኢራን አቋም በእሥራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ዘንድ አመኔታ ኔታንያሁ ቀደም ሲልም በዋሽንግተን ከዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ጋ ባደረጉት ውይይት ላይ ዩኤስ በዚችው ሀገር ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንድታጠናክር ጠይቀዋል። ዩኤስ እና እሥራኤል ኢራን መርሀግብርዋን ምናልባት ለአቶም ጦር መሣሪያ ምርት ልትጠቀምብት እንደምትችል ነው በተደጋጋሚ የሚያስጠነቅቁት። ግን አዲሱ የኢራን ፕሬዚደንት ሀሳን ሮሀኒ ሀገራቸው የኑክልየር መርሀግብርዋን ለሰላማዊ ጠቀሜታ እንጂ የኑክልየር ጦር መሣሪያ ምርት እንደማታውለው እና በዚሁ ሰበብ ከምዕራቡ ጋ ለተፈጠረው ውዝግብ መፍትሔ ለማፈላለግ ዝግጁ አነደሆነች ሲገልጹ ተሰምቶዋል። ይኸው የኢራን አቋም በእሥራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ዘንድ አመኔታ አላገኘም? ሀይፋ ለሚገኘው ዘጋቢያችን ግርማው አሻግሬ ቀደም ሲል በስልክ ያቀረብኩለት ጥያቄ ነበር።

Hassan Rohani 26.11.2
ምስል picture alliance/Newscom

ግርማው አሻግሬ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ