1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢህአዴግ እና የግንቦት 20 ሀያኛ ዓመት

ቅዳሜ፣ ግንቦት 20 2003

የኢትዮጽያ ህዝባዊ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር - ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ይመራ የነበረውን ወታደራዊ ሶሻሊስታዊ የደርግ ስርአት አስወግዶ ስልጣን ከያዘ ዛሬ ልክ ሀያ ዓመቱን ደፈነ።

https://p.dw.com/p/RQbh
ምስል AP Graphics/DW Fotomontage


ዕለቱ በመላ ኢትዮጵያ በደመቀ ስርዓት እየተከበረ ነው። የኤርትራ ህዝባዊ ግንባር ሀርነት ኤርትራ፡ ያኔ በምህጻሩ ኢፒኤልኤፍ ይባል የነበረው ኃይልም በድል አስመራ የገባበት ሀያኛ ዓመት ባለፈው ማክሰኞ በደመቀ ስነ ስርዓት ተከብሮ ዉሎአል። ኤሃዴግና የኤርትራ ህዝባዊ ግንባር ሀርነት ኤርትራ በደርግ አንጻር ድል ተቀዳጅተው አዲስ አበባ እና አስመራ በድል በገቡበት ጊዜ የሁለቱ አገሮች ህዝቦች ድሉን እንደ አዲስ ጅምር ነበር የተመለከቱት። ድሉ በሁለቱ አገሮች የሰላም እና የዴሞክራሲ ጮራ እንደፈነጥቀና ልማትን እንደሚያሳድግ ነበር የተሰማቸዉ። ያ የህዝቦች ተስፋ ገሃድ ስለመሆን አለመሆኑ እንደተለያዩት ቡድኖች አመለካከቱም የተለያየ ነዉ። አንዳንዶች ያለፉትን ሃያ አመታት ሂደት አጥጋቢ ሆኖ ሲያገኙት ሌሎች ደግሞ ያ ተስፋቸዉ መና እንደቀረ ይናገራሉ። ተቃዋሚ ቡድኖች በተለይ የሰሜን አፍሪቃ ዓብዮት ከፈነዳ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ኢህአዴግ ስልጣኑን እንዲለቅ በመጠየቅ በቃ የሚል ህዝባዊ ዓመጽ እንዲካሄድ ቅስቀሳ ጀምረዋል።

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ