አፍሪቃና የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች መግለጫ፣
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16 2003ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን፣ ጋናንና ሴራሊዮንን ባለፈው ሳምንት የጎበኙት የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት (ቡንደስታኽ) አባላት ወደ በርሊን እንደተመለሱ በሰጡት መግለጫ ላይ፣ የአፍሪቃን የፀጥታ ችግር ለማስወገድ፣ ፀጥታ አስከባሪ ሠራዊት ከመላክ ፣ ህዝቡን፣ ስለሰላማዊ ኑሮ ማስተማር እንደሚቀልና በወጪም ረገድ ረከስ እንደሚል ተናገረዋል። ከአፍሪቃ መሪዎችም ጋር የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተው የተወያዩት መማክርት፣ በኢትዮጵያ፣ የዴሞክራሲ መብቶች እንዲከበሩ መጠየቃቸውንም ገልጸዋል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል---
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ