1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዳጊው የፊልም ተዋናይ

እሑድ፣ የካቲት 17 2011

ታዳጊ የፊልም ተዋናይ ነው። እዮብ ዳዊት። 23 ፊልሞችን ተውኗል። አዲስ በሚወጡ ፊልሞች ላይ እሱን ማየታችን አዲስ አይሆንም።

https://p.dw.com/p/3DtVC
Filmstill | Mike Leigh: Mr. Turner (2014)
ምስል picture-alliance/dpa/epa/Cannes Film Festival

እዮብ ዳዊት የፊልም ተዋናይ

በፊልም ሥራዎች ላይ መተወን የጀመረው በዘጠኝ ዓመቱ ነው። ላለፉት ሰባት ዓመታትም 23 ፊልሞችን ተውኗል። ያልታሰበው መጀመሪያ በትወና የተሳተፈበት ፊልም ነው፤ በዘጠኝ ዓመቱ። ብላቴና የሚለው ደግሞ ሁለተኛው። የ16 ዓመቱ ታዳጊ ወጣት እዮብ ዳዊት። አጼ ማንዴላ፣ ደስ ሲል፣ የልጅ ሀብታም፣ እስክትመጪ ልበድ፣ ያልታሰበው፣ የአራዳ ልጅ ፣ ይመችሽ የአራዳ ልጅ 2፣ ያበደች የአራዳ ልጅ 3፣ ከተወነባቸው ፊልሞች ጥቂቶቹ ናቸው።  ከአዳጊው ወጣት የፊልም ተዋናይ እዮብ ዳዊት ጋር የነበረንን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ። 

 

ነጃት ኢብራሂም 

ሸዋዬ ለገሰ