1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዋ አምባሳደር በጀርመን

ረቡዕ፣ ሰኔ 5 2011

አምባሳደር ሙሉ የሹመት ደብዳቤያቸዉን ባቀረቡበት ወቅት የኢትዮጵያና የጀርመን ወዳጅነት ተጣንክሮ እንዲቀጥል ሁለቱም የየበኩላቸዉን እንደሚጥሩ አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/3KFif
Deutschland Akkreditierung von H.E. Mulu Solomon Bezunehbei Bundespräsident Steinmeier
ምስል Ethiopian Embassy in Berlin

የአምባሳደር ሙሉ የሹመት ደብዳቤ

በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነዉ የተሾሙት ወይዘሮ ሙሉ ሠለሞን የሹመት ደብዳቢያቸዉን ትናንት ለጀርመኑ ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር አቅርበዋል። አምባሳደር ሙሉ የሹመት ደብዳቤያቸዉን ባቀረቡበት ወቅት የኢትዮጵያና የጀርመን ወዳጅነት ተጣንክሮ እንዲቀጥል ሁለቱም የየበኩላቸዉን እንደሚጥሩ አስታዉቀዋል። ወይዘሮ ሙሉ በአምባሳደርነት ተሹመዉ ጀርመን የመጡት ባለፈዉ ሚያዚያ መጀመሪያ ነበር። ሥለአምባሳደርዋ ተልዕኮና ኃላፊነት ከበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ባጭሩ ተነጋግረን ነበር።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ