1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የኔቶ ዋና ጸሐፊ እና ዕቅዳቸዉ

ሰኞ፣ መስከረም 26 2007

ሚስተር የንስ ስቶልቴንበርግ ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ 28 አባል መንግሥታት የሚገኙበትን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ኔቶን የመምራትS ስራቸውን በይፋ መረከባቸው ይታወሳል። ስቶልቴንበርግ ግዙፉ የምዕራባዉያን ወታደራዊ ግንባር ከዚህ ቀደም በበላይነት የመሩት አንደርስ ፎኽ ራስሙሰንን ነው የተኩት።

https://p.dw.com/p/1DREV
NATO Logo
ምስል picture-alliance/dpa

አዲሱ የኔቶ መሪ ገና በለጋ እድሜያቸዉ የቬትናትም ጦርነትና አሜሪካንን በመቃወም ወደፖለቲካዉ ዓለም መግባታቸዉ ይነገራል። የኖርዌይ ዜጋ የሆኑት ስቶልቴንበርግ በተለያዩ የስልጣን ርከኖች ላይ በመሆን ሀገራቸዉ ያገለገሉ ሲሆን በተመድ ዉስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ ሠርተዋል። ፖለቲከኛዉ ከሩሲያዉ መሪ ፕሬዝደንት ቪላድሚር ፑቲን ጋ መልካም ግንኙነት ካላቸዉ ጥቂት የኔቶ አባል ሃገራት መሪዎች አንዱ መሆናቸዉ ይነገራል። በድርጅቱና ሩሲያ ግንኙነት ላይ ለዉጥ ያመጡ ይሆን?

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ