1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አደጋ ላይ የወደቀዉ የኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 3 2011

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ዓመት በመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ላይ ባደረገው ከፍተኛ መሻሻል የኋሊት የመቀልበስ አደጋ ተጋርጦበታል ሲል የዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አሳሰበ። ሰሞኑን ጋዜጠኞችን ማሰሩና የሐገሪቱን መከላከያ ሚንስቴር ወታደራዊ ሚስጥር አወጡ ያላቸዉን ጋዜጠኞች እንደሚከስ ማስታወቁ ለፕረስ ነፃነት አደገኛ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3LohK
Amnesty international
ምስል picture-alliance/dpa/W.Kumm

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ዓመት በመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ላይ ያደረገው ከፍተኛ መሻሻል የኋሊት የመቀልበስ አደጋ ተጋርጦበታል ሲል የዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አሳሰበ። ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ዛሬ ባሰራጨዉ ዘገባ እንዳለዉ መንግሥት ሰሞኑን ጋዜጠኞችን ማሰሩና የሐገሪቱ መከላከያ ሚንስቴር ወታደራዊ ሚስጥር አወጡ ያላቸዉን ጋዜጠኞች እንደሚከስ ማስታወቁ ለፕረስ ነፃነት አደገኛ ነዉ።  በምስራቅ አፍሪቃ የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ተጠሪ ጆአን ንያንዩኪ እስሩና የመክሰስ ዛቻዉ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በኢትዮጵያ የታየዉን የፕሬስ ነፃነት የሚደፈጥጥ፣ ሃገሪቱንም ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ  የሚያመራት እንደሆነ አመልክተዋል።  የድርጅቱ ዋና ተጠሪ የታሰሩ ጋዜጠኞች ሁሉ መፈታት አለባቸዉ ፤ የተመሰረተባቸዉ ክስም ዉድቅ መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል። አምንስቲ እንዳለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት መፈንቅለ መንግሥት ካለዉ የባለስልጣናት ግድያ በኋላ ሦስት ጋዜጠኞች ታስረዋል። ከሦስቱ ሁለቱ በአሸባሪነት ተከስሰዋል።

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ