1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አደገኛ የኢንተርኔት ጠላቶች ይፋ ሆኑ

ዓርብ፣ መጋቢት 4 2001

ኢትዮጵያ፤ በውነቱ ክትትል ከሚደረግባቸው ሀገራት አንዷ ልትሆን ትችል ነበር ብለን ነው የምናያት። ምክንያቱም በርካታ በኢንተርኔት የሚወጡ የብሎግ ፅሁፎች ታግደው ነበርና። ሆኖም ባለስልጣናቱ እገዳውን እንዳነሱት አውቀናል።

https://p.dw.com/p/HBM0
ኢንተርኔትን ያለገደብ
ኢንተርኔትን ያለገደብምስል AP
ነፃ የኢንተርኔት መረጃ ፍሰትን አስመልክቶ፤ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች፤ በእንግሊዘኛ ምህፃሩ Reporters without Borders ትናንት መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው የኢንተርኔት ጠላቶች ሲል አስራ ሁለት ሀገራትን ይፋ አድርጓል። ይህን አስመልክቶ በድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የኢንተርኔት ነፃነት ክፍል ሀላፊ ሚስ ክሊቺልድ ሉኩዝ የሚሉት ይኖራል።