1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሮፕላኑ የወደቀበት ሥፍራ

እሑድ፣ መጋቢት 1 2011

በአካባቢዉ የነበሩ ሰዎች እንዳሉት አዉሮፕላኑ ሲወድቅ አካባቢዉ በከፍተኛ ድምፅ ታዉኮ ነበር።አዉሮፕላኑ ከምድር ጋር በተላተመበት ስፍራ ሰፊ ጥቁር ጉርጓድ መፈጠሩን የዓይን ምስክሮቹ ገልጠዉ፣ አካባቢዉ በስብርባሪና ምናልባት በተሳፋሪዎች የሰዉነት ቁጥርራጭ  መሞላቱን አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/3EklI
Äthiopien Mehr als 150 Tote bei Flugzeugabsturz
ምስል Reuters/T. Negeri

(Q&A) Ethiopian flight 302 - MP3-Stereo

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በረራ ጀምሮ የነበረዉ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 302፣ A 737 MAX 8 አዉሮፕላን ዛሬ ጠዋት  የተከሰከሰዉ ከደብረ ዘይት ወይም ቢሾፉቱ ወጣ ብሎ ኢጄሬ ወይም ገረቡላ በተባለዉ የገጠር አካባቢ ነዉ።አደጋዉ ሲደርስ በአካባቢዉ የነበሩ ሰዎች እንዳሉት አዉሮፕላኑ ሲወድቅ አካባቢዉ በከፍተኛ ድምፅ ታዉኮ ነበር።አዉሮፕላኑ ከምድር ጋር በተላተመበት ስፍራ ሰፊ ጥቁር ጉርጓድ መፈጠሩን የዓይን ምስክሮቹ ገልጠዉ፣ አካባቢዉ በስብርባሪና ምናልባት በተሳፋሪዎች የሰዉነት ቁጥርራጭ  መሞላቱን አስታዉቀዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ 

ልደት አበበ