1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሮጳና ጀርመን

ሐሙስ፣ ጥቅምት 5 2002

ስምምነቱ «ሉአላዊነቴን ይጋፋል» ብላ የምትፈራዉ ቼክ ሪፐብሊክ ግን እስካሁን እንዳፈነገጠች ነዉ።የሐገሪቱ ፕሬዝዳት ቫክላቭ ክላዉስ ሰነዱን በፊርማቸዉ ለማፅደቅ ተጨማሪ ቅድመ-ሁኔታዎችን እየደረደሩ ነዉ

https://p.dw.com/p/K71V
የሊዝበኑ ዉል ተቃዋሚዎችምስል Alen Legovic

አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን ለዛሬዉ በሁለት ጉዳዮች ላይ ያጠነጥናል።አዉሮጳ-ሕብረቷንና ጀርመን-መንግሥቷን።አብራችሁን ቆዩ።

----------------------------------------

የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐራትን ባንድ ወጥ ሕግ ለማስተዳደር የሚደረገዉ ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥሩ እመርታ እያሳየ ነዉ።ወይም መስሏል።ሃያ-ሰባቱን አባል ሐገራት ያስተሳስራል የተባለዉን የሊዝበን ሥምምነት የአየር ላንድ ሕዝብ በቅርቡ በድምፅ ካፀደቀዉ ወዲሕ እስካሁን ዉሉን ለመቀበል ስታቅማማ የነበረችዉ ፖላንድ ተቀብላዋለች።የሐገሪቱ ፕሬዝዳት ሌኽ ካሽዲስኪ ወሉን ባለፈዉ ሳምንት አፅድቀዉታል።ስምምነቱ «ሉአላዊነቴን ይጋፋል» ብላ የምትፈራዉ ቼክ ሪፐብሊክ ግን እስካሁን እንዳፈነገጠች ነዉ።የሐገሪቱ ፕሬዝዳት ቫክላቭ ክላዉስ ሰነዱን በፊርማቸዉ ለማፅደቅ ተጨማሪ ቅድመ-ሁኔታዎችን እየደረደሩ ነዉ።
ያም ሆኖ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ እንደታዘበዉ፥-የሊዝበኑን ሥምምነት ገቢር የማድረጉ ሒደት ቀጥሎ የሰሞኑ ክርክር ወደፊት በሚዋቀረዉ የሕብረቱ ተቋም መሪ ማንነት ላይ አተኩሯል።

---------------------------------

ጀርመን እንደ አዉሮጳ ሕብረት ትልቅ አባል ሐገር ብራስልስ የሚደረገዉ ክርክር ዋና ተሳታፊ ሆና እዚሕ በዉስጧ ደግሞ በተጣማሪ መንግሥት ምሥረታ ዉይይት፣ ክርክር ተጠምዳለች።ዉይይት፥ ክርክሩ ለፌደራላዊዉ መንግሥት ብቻ ሳይሆን ለክፍለ-ሐገራት መስተዳድርም የሚደረግ ነዉ።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ-ሚካኤል ጉዳዩን ተከታትሎታል።

አዉሮጳና ጀርመን የእስካሁኑ ነበር።ሳምንት በተመሳሳይ ጊዜ ከሌላ ዝግጅትና አዘጋጅ ጋር እንጠብቃችኋለን።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ደሕና አምሹ።

ገበያዉ ንጉሴ እና ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ