1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሮፌሰር ክፍሌ ስላሴ ብፅዓት

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 7 2011

ፕሮፌሰር ክፍሌ ፈረንሳይ ሐገር ተምረዉ ፓሪስ-ፈረንሳይ ዉስጥ በዩኒቨርስቲ አስተማሪነት፤ በተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO) ባልደረባነት፣ በጋዜጣ ፀሐፊና በቴሌቬዥን ጣቢዎች ተንታኝነት ሠርተዋል

https://p.dw.com/p/3NqYV
Verabschiedung Professor Kifile Sillasie Bitsat
ምስል DW/H. Tiruneh

ፕሮፌሰር «ክፍሌ ኢንሳይክሎፒዲያ ነበር»

በጥናትና ምርምር ሥራቸዉ፣በምሁራዊ ትንታኔቸዉ፣ አዉሮጳና አፍሪቃን፣በተለይም ኢትዮጵያንና ፈረንሳይን በማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉት ኢትዮጵያዊ ምሁር ፕሮፌሰር ክፍሌ ስላሴ ብፅዓት በቅርቡ ፓሪስ ፈረንሳይ ዉስጥ አርፈዋል።የፍልስፍና፤የታሪክ፤ የፖለቲካና የባሕል ምሕሩ ፕሮፌሰር ክፍሌ ፈረንሳይ ሐገር ተምረዉ ፓሪስ-ፈረንሳይ ዉስጥ በዩኒቨርስቲ አስተማሪነት፤ በተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO) ባልደረባነት፣ በጋዜጣ ፀሐፊና በቴሌቬዥን ጣቢዎች ተንታኝነት ሠርተዋል።ሕይወታቸዉ እስካለፈበት ጊዜ ድረስም ራሳቸዉ የመሰረቱት የፓን አፍሪቃን አፕላይድ ሪሰርች ኢኒሼየቲቭ የተባለዉን መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም በኃላፊነት መርተዋል።የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን የፕሮፌሰር ክፍሌን ማንነትና ሥራን ይቃኛል።

ሃይማኖት ጥሩነሕ 

ነጋሽ መሐመድ