1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሎ ነፋስ በመካከለኛዉ ምሥራቅ

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 4 2007

ሶሪያን፤ ሊባኖስን እስራኤልንና ቆጵሮስን ያዳረሰዉ አዉሎ ነፋስ በትንሹ ስምንት ሰዎችን ገድሏል። በመቶ የሚቆጠሩትን በሽታ ላይ ጥሏል።

https://p.dw.com/p/1GTp4
አዉሎ ነፋስ በመካከለኛዉ ምሥራቅ
ምስል Hamad Olayan/AFP/Getty Images

[No title]

በመካከለኛዉ ምሥራቅ አካባቢ ባለፉት ተከታታይ ወራት የተከሰተዉ ከፍተኛ ሙቀት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል። አለቅጥ የናረዉ የሙቀት መጠን ሰሞኑን ጋብ ማለቱ ከመሰማቱ አካባቢዉ በሌላ ተፈጥሯዊ መቅሰፍት ተመትቷል። አዉሎነፋስ። ሶሪያን፤ ሊባኖስን እስራኤልንና ቆጵሮስን ያዳረሰዉ አዉሎ ነፋስ በትንሹ ስምንት ሰዎችን ገድሏል። በመቶ የሚቆጠሩትን በሽታ ላይ ጥሏል።የእየሩሳሌሙ ወኪላችንን ዜናነሕ መኮንን እንደሚለዉ የዘንድሮዉን ዓይነት መቀትና አዉሎ ነፋስ በአካባቢዉ የሰባ አምስት ዓመት ታሪክ ታይቶ አይታወቅም።

ዜናነሕ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ