1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አወዛጋቢው የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን

ሰኞ፣ ግንቦት 4 2006

ማስተር ፕላኑ የኦሮምያ ክልልን ጥቅም ያስቀራል የአካባቢውን ገበሪ ያፈናቅላል የሚሉና የመሳሰሉ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩበት ነው ። መንግሥት ግን ማስተር ፕላኑ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮምያ ልዩ ዞን ከተሞችም ከአዲስ አበባ ጋር አብረው እንዲያድጉ ታስቦ ነው ይላል ።

https://p.dw.com/p/1BxNE
Addis Abeba
ምስል picture alliance / landov

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኘው የኦሮምያ ልዩ ዞን ጋር የተቀናጀው አስረኛው የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን የኦሮምያ ክልልን ጥቅም ያስቀራል የአካባቢውን ገበሪ ያፈናቅላል የሚሉና የመሳሰሉ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩበት ነው ። መንግሥት ግን ማስተር ፕላኑ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮምያ ልዩ ዞን ከተሞችም ከአዲስ አበባ ጋር አብረው እንዲያድጉ ታስቦ ነው ይላል ። በዚህ እቅድና ተቃውሞ ሳቢያ ባለፈው ሳምንት የሰዎች ህይወት አልፏል የቆሰሉ ና የታሰሩም አሉ ።ንብረትም ወድሟል ። የግጭት መንስኤ ሆኗል የተባለው የተቀናጀው ማስተር ፕላንና የተነሳበት ተቃውሞ የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው ።

ሂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ