1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አኗኗራችን እና ጤናችን

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 8 2011

በዕድሜ የገፉ ሰዎችን ብቻ ያሰጋሉ የሚባሉት የማይተላለፉ በሽታዎች አሁን የዕድሜ ገደብ ሳያግዳቸው ጉዳት ማድረሳቸው ይነገራል። የልብ፣ የስኳር፣ የደም ዝውውር መስተጓጎል፣ የደም ግፊት፣ እንዲሁም ካንሰር እና የመሳሰሉት በሽታዎች በአብዛኛው የአመጋገብ፣ የእንቅስቃሴ ጉድለት እንዲሁም የስነልቡና አለመረጋጋት ውጤቶች መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ።

https://p.dw.com/p/3Gtdw
Gericht | Zoodles | Gemüsespaghetti
ምስል imago/Westend61

አኗኗራችን እና ጤናችን

 የዓለም የጤና ድርጅት እነዚህ ህመሞች የሚያደርሱትን ጉዳት አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ሰዎች በየትኛውም የዕድሜ ክልል ቢሆኑ፣ በየትኛውም ሀገር እና አካባቢ ቢኖሩ የአኗኗር ሁኔታቸው በተለያዩ ምክንያቶች ሲለወጥ፤ ለበሽታዎቹ መጋለጣቸው እንደማይቀር ያመለክታል። ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ በቂ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ትንባሆ ማጨስ እንዲሁም የአልክሆል መጠጥን በአደገኛ መልኩ መጠቀም በበሽታዎቹ የመያዝን፤ ምልክቱ ቀድሞ ካለም ደግሞ የማባባስን አጋጣሚ እንደሚያመቻችም ይገልጻል። እንደ የዓለም የጤና ድርጅት ከሆነም በሽታው ያለእቅድ ከሚደረግ የከተሞች መስፋፋት እና ዓለም አቀፋዊነት ካለው የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ጋር ይያያዛል። ይህም ማለት በእግር ረዥም መንገድ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ይህን ትተው ጉዟቸው በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲወሰን፤ በየጊዜው ትኩስ እና ቤት ውስጥ የተዘጋጁ ምግቦችን ከመመገብ ይልቅ ለረዥም ጊዜ እንዲቆዩ ተደርገው የታሸጉ ምግቦችን መመገብ ሲያዘወትሩ፤ መጠጥ እና ትንባሆ ማጨሱም ሲጠና ሰዎች እነዚህ በሽታዎች ወደራሳቸው እየጋበዙ መሆኑን ልብ እንዲሉት ይመክራል። ባለፈው ሳምንት ስለጤናማ አኗኗር ዘይቤ ሙያዊ ማብራሪያዎችን የሰጡን የዝግጅታችን ቤተኞች የሆኑት የውስጥ ደዌ ከፍተኛ ሃኪም ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ እና የስነምግብ ባለሙያው አቶ አብነት ተክሌ፤ ጤናማ አመጋገብ እና ተቃራኒው እንዴት እንደሆነ፣ መመገብ የሚገባን የምንፈልገውን ብቻ ሳይሆን ለሰውነታችን የሚያስፈልጉትን መሆኑን አብራርተዋል። ያልተስተካከል አመጋገብም የጤና ችግር እንደሚያስከትልም በመጥቀስ ዘርዝረዋል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ማዕቀፉ ያድምጡ፤

Symbolbild Selbstläufer
ምስል Colourbox

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ