አነጋጋሪው የጀርመን ብሔረተኛ ፓርቲ NPD1 ጳጉሜን 2003ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 1 2003ከትናንት በስተያ በጀርመኑ የ Mecklenburg-Vorpommern ፌደራዊ ክፍለ ግዛት በተካሄደ ምርጫ ፣ መፍቅሬ ናዚ የሚባለው የጀርመን ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በጀርመንኛው ምህፃር NPD ለሁለተኛ ጊዜ የምክር ቤት መቀመጫ ለማግኘት የሚያበቃ ድምፅ ማግኘቱ እዚህ ጀርመን እያነጋገረ ነው ።https://p.dw.com/p/RkBoኤርቪን ሴለሪንግምስል dapdማስታወቂያNPD የጀርመንን ህገ መንግሥት የሚፃረር ፓርቲ ነው ሲሉ የሚከራከሩት ዋና ዋናዎቹ የጀርመን ፓርቲዎች ፤ ከዚህ ቀደም ሲያደርጉ እንደቆዩት ሁሉ ፓርቲው እንዲታገድ ዳግም ጥሪ ማስተላለፍ ጀምረዋል ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን የዚህን ፓርቲ መርሆችና ፣ ፓርቲው እንዲታገድ የተደረጉ ጥረቶችንና ሙከራዎቹም ያልሰመሩበትን ምክንያት ይመለከታል ። ሂሩት መለሰሸዋዪ ለገሰ