1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ አስራት ጣሴ ተፈረደባቸዉ

ዓርብ፣ የካቲት 7 2006

በፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሠረት አቶ አስራት አምስት ወራት እስራት ተቀጥተዉ፥ በሁለት ዓመት ገደብ ተለቀዋል።የአቶ አስራት ጠበቃና ፓርቲያቸዉ ብይኑን ተቃዉመዉ ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/1B9Vt
ምስል AP

የኢትዮጵያ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ አስራት ጣሴ የአምስት ወር እስራት በሁለት ዓመት ገደብ ተፈረደባቸዉ።ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ የኢትዮጵያ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዘጠነኛ ችሎት አቶ አስራት ጣሴን በመፅሔት ባሳተሙት ፅሁፍ ጥፋተኛ ብሎ ፈርዶባቸዋል።በፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሠረት አቶ አስራት አምስት ወራት እስራት ተቀጥተዉ፥ በሁለት ዓመት ገደብ ተለቀዋል።የአቶ አስራት ጠበቃና ፓርቲያቸዉ ብይኑን ተቃዉመዉ ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ