1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 አቶ በረከት አቶ ታደሰ ባሕርዳር ይዳኛሉ

ረቡዕ፣ ጥር 15 2011

የአማራ መስተዳድር የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ዝግአለ ገበየሁ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት ሁለቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የታሰሩት ጥረት የተሰኘዉን የኩባንዮች ስብስብ በማክሰራቸዉ ነዉ

https://p.dw.com/p/3C3vV
Äthiopien Regierungsvertreter
ምስል DW/Tesfalem Waldyes

በቁጥጥር ሥር የዋሉት እነ አቶ በረከት ስምዖን ወደ ባሕር ዳር ተወስደዋል


የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢሕድን)ና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መሥራቾች አቶ በረከት ስሞዖንና አቶ ታደሰ ካሳ የታሰሩትም፣የሚዳኙትም አማራ ክልል እንደሆነ የክክሉ ባለሥልጣን አስታወቀ።የአማራ መስተዳድር የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ዝግአለ ገበየሁ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት ሁለቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የታሰሩት ጥረት የተሰኘዉን የኩባንዮች ስብስብ በማክሰራቸዉ ነዉ።ድሮ ኢሕዴን፣ በመሐሉ ብአዴን፣ በቅርብ ደግሞ አዴፓ በሚሉ ምሕፃረ-ቃላት የሚጠራዉ የአማራ ክልክል ገዢ ፓርቲ የመሠረተዉና የሚቆጣጠረዉ ድርጅት የአስራ-ሠባት አምራችን ነጋዴ ኩባንዮች ባለቤት ነዉ።

 አለምነዉ መኮንን ልኮልናል።

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ