1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አባ ሙሴ እና የበጎ አድራጎት ሥራቸው

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 14 2007

በሺህዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የሚረዱት የ40 ዓመቱ አባ ሙሴ እጎአ ለ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማት ከታጩት ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ተዘግቧል ። አባ ሙሴ ለዚህ ሽልማት መታጨታጨታው ክብሩ ለርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለአፍሪቃውያንም ጭምር ነው ይላሉ ።

https://p.dw.com/p/1G2Je
Mussie Zerai Gründer Hilfswerk Habeshia
ምስል picture-alliance/dpa/B. Doppagne

አባ ሙሴ ዘርዓይ እና የበጎ አድራጎት ስራቸው

አባ ሙሴ ዘርዐይ እዚህ አውሮፓ በመንፈሳዊ አገልግሎት የተሰማሩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሃይማኖት አባት ናቸው ። በአሁኑ ጊዜ ስዊዘርላንድ ለሚኖሩ ኤርትራውያን ኢትዮጵያውያን ካቶሊኮች መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው ። ከዚያም ቀደም ሲል በቀሰሱበት ና ከፍተኛ ትምህርታቸውን በተከታተሉባት በኢጣልያ ተመሳሳይ አገልግሎት ላይ ነበሩ ። ከዛሬ 9 ዓመት ወዲህ ደግሞ በመንፈሳዊው አገልግሎት ብቻ ሳይወሰኑ በግበረ ሰናይ ድርጅታቸው አማካይነት በሜዲቴራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ የሚሰደዱ አፍሪቃውያን እየታደጉ ነው ። የዛሬ 23 ዓመት በመጡበት በኢጣልያ የመሰረቱት ኤጀንስያ አበሻ የተሰኘው ይኽው ድርጅታቸው በአደገኛ የባህር ጉዞ የሚሰደዱ በርካታ ወጣቶችን ህይወት አትርፏል። እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ስደተኞች ልዩ ልዩ ድጋፎችን በመስጠት ላይ ይገኛል ።
ምንም እንኳን አባ ሙሴ ኤጀንስያ አበሻን በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር 2006 ዓም ቢያቋቁሙም ስደተኞችን መርዳት የጀመሩት ግን ከዚያ አስቀድሞ ነበር።



ድርጅታቸው ኤጀንሲያ አበሻ እነዚህን ሥራዎች የሚያከናውነው በበጎ ፈቃደኖች አገልግሎት ና የገንዘብ እርዳታ እንደሆነ አባ ሙሴ ያስረዳሉ ።ርሳቸው እንደሚሉት ድርጅታቸው ከመንግሥትም ሆነ ከትላልቅ ድርጅቶች ያሚያገኘው ገንዘብ የለም ። አባ ሙሴ ተወልደው ያደጉት የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አስመራ ኤርትራ ነው ። በጎርጎሮሳውያኑ 1992 ዓም ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ቪዛ ካገኑ በኋላ በ17 ዓመታቸው ጣሊያን ይኖሩ ወደ ነበሩት አባታቸው ሄዱ ። በጣልያን ለተወሰኑ ዓመታት እየሰሩም እየተማሩም ከቆዩ በኋላ 26 ዓመት ሲሞላቸው ቅስና ተቀብለው ገዳም ገቡ ። የገዳም ህይወትን ከመረጡ በኋላ ዩኒቨርስቲ በመግባት ትምህርታቸውን ቀጥለው በፍልስፍናና በስነ መለኮት የባችለር ዲግሪ አግኝተዋል ። ከዚያም በመቀጠል በስነ መለኮት ትምህርት ስር የማህበራዊና የሞራል ትምህርትም ተከታትለዋል ። አባ ሙሴ እንደሚሉት መንፈሳዊው ህይወት ውስጥ የመግባት ፍላጎቱ የነበራቸው ገና ታዳጊ ወጣት ሳሉ አንስቶ ነበር ።
አባ ሙሴ ከጎርጎሮሳዊው 2006 ዓም ወዲህ ይበልጡን የሚታወቁት በበጎ አድራጎት ተግባራቸው ነው ። ርሳቸው እንደሚሉት ይሄ ከተሰማሩበት መንፈሳዊ አገልግሎት ተለይቶ የሚያታይ አይደለም።
በሺህዎች የሚዎጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የሚረዱት የ40 ዓመቱ አባ ሙሴ እጎአ ለ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማት ከታጩት ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ተዘግቧል ። አባ ሙሴ ለዚህ ሽልማት መታጨታጨታው ክብሩ ለርሳቸው ብቻ
በአሁኑ ጊዜ በአደገኛ የባህር ጉዞ ወደ አውሮፓ የሚሰደዱ ሰዎችን ለመርዳት የሚደረገው ጥረት ቀድሞም ተጀምሮ ቢሆን የበርካታ ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ይቻል ነበር ይላሉ አባ ሙሴ ። ወደፊት መንግሥታት ችግሩን ለመፍታት ይበልጥ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል ።

Mussie Zerai Gründer Hilfswerk Habeshia
ምስል Vincenzo Pinto/AFP/Getty Images

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ