አቃቢተ ህግ ቤንሱዳ ቃለ መሃላ ፈፀሙ
ዓርብ፣ ሰኔ 8 2004ማስታወቂያ
ህግ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል ። እጎአ ከ 2004 ዓም አንስቶ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሉዊስ ሞሬኖ ኦካምፖ አስረክበዋል ። ቤንሱዳ የአለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ና አፍሪቃዊት አቃቢተ ህግ ናቸው ። የሥራ ዘመናቸውን ፈፅመው ዛሪ ሃላፊነታቸውን ለቤንሱዳ አስረክበዋል ። ቤንሱዳ የአለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ና አፍሪቃዊት አቃቢተ ህግ ናቸው ። ለዚህ ሥልጣን የበቁትም ፍርድ ቤቱ የተመሰረተበትን የሮሙን ውል በፈረሙ 121 ሃገሮች ተመረጠው ነው ። አቃቢተ ህግ ቤንሱዳ የዘር ማጥፋት፣ የጦር እና በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ክስ የተያዙባቸውን የ 7አፍሪቃ አገሮች 15 ጉዳዮችን የመርመር ሃላፊነት ተረክበዋል ። እጎአ በ2003 የተቋቋመው ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት እስካሁን 20 የእስር ማዘዣዎችን ቢቆርጥም እስካሁን የታሰሩት ግን 6 ተጠርጣሪዎች ብቻ ናቸው ። በፍርድ ቤቱ ከሚፈለጉት ውስጥ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ና የጌታ ተከላካይ ጦር የተባለው የኡጋንዳውየአማፅያን ቡድን መሪ ጆሴፍ ኮኒ ይገኙበታል ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ