1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ላይ የህዝብ አስተያየት

ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2011

DW ዶቼቬለ ከደቡብ ክልል አስተያየታቸውን ከጠየቃቸው አንዱ ፣ምክር ተግሳጽ እና ይቅርታን ያካተተውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር አወድሰው ለውጡን ተቋማዊ በማድረግ ወደታችኛው የህብረተሰብ ክፍልም እንዲደርስ እንዲጥሩ ጠይቀዋል።ሌላ አስተየት ሰጭ በርሳቸው የሥልጣን ዘመን በተለያዩ ዘርፎች ነጻነቶች መገኘታቸውን አስታውሰው ሊደገፉ ይገባል ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3GBor
Abiy Ahmed Äthiopien
ምስል Reuters/T. Negeri

አእተያየት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ላይ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ትናንት በአዲስ አበባው ሚሊኒየም አዳራሽ የአንድ ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው በተዘከረበት መርሃ ግብር ላይ ባሰሙት ንግግር ባለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፤ በፓለቲካ፣ በማኅበራዊ ዘርፎች ተገኙ ያሏቸውን ለውጦች ዘርዝረዋል። በለውጡ ሂደት የደገፏቸውን አመስግነዋል። ህዝብ ጠብቆ ላላከናወኗቸው ጉዳዮችም ይቅርታ ጠይቀዋል። የትናንቱ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ንግግር የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል። በንግግሩ ላይ DW ዶቼቬለ ከደቡብ ክልል አስተያየታቸውን ከጠየቃቸው አንዱ ፣ምክር ተግሳጽ እና ይቅርታን ያካተተውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር አወድሰው ለውጡን ተቋማዊ በማድረግ ወደታችኛው የህብረተሰብ ክፍልም እንዲደርስ እንዲጥሩ ጠይቀዋል። ሌላ አስተየት ሰጭ ደግሞ በርሳቸው የሥልጣን ዘመን በተለያዩ ዘርፎች ነጻነቶች መገኘታቸውን አስታውሰው ሊደገፉ ይገባል ብለዋል። ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዘገባ አለው።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ