1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አምነስቲ ሊብያን ወቀሰ

ረቡዕ፣ ሰኔ 3 2001

ሊብያ በሀገርዋ በአፍሪቃውያን ስደተኞች ላይ የምትፈፅመዉን ተግባር ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የትሪፖሊ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አጥብቆ ነቀፈ።

https://p.dw.com/p/I72O
ምስል AP

የሊብያዉ መሪ በኢጣልያ ጉብኝት ሊጀምሩ አንድ ቀን ሲቀራቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ፡ የኢጣልያ መሪዎች ሊብያ የሰብዓዊ መብቶችን እንድታከብር ተጽዕኖ እንዲያሳርፉ አሳስቦዋል። ከዚህ በተጨማሪም ወደ አውሮጳ በህገ ወጥ መንገድ በትናንሾቹ ጀልባዎች ሊገቡ የሚሞክሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን በግዳጅ ወደ ሊብያ ለመመለስ ሁለቱ ሀገሮች ቀደም ሲል የደረሱትን ስምምነት ወቅሶዋል። ሀና ደምሴ

HD/AA/SL